1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

ትራምፕ በቢቢሲ ላይ እስከ 5 ቢሊየን ዶላር የሚያስቀጣ ክስ ሊመሰርቱ ነው

ቅዳሜ፣ ኅዳር 6 2018

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከ1 ቢሊዮን እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የጉዳት ካሳ የሚጠይቅ ክስ ቢቢሲ ላይ እንሚመሰርቱ ገለፁ።ትራምፕ ክሱን በሚቀጥለው ሳምንት ሊመሰርቱ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ቢቢሲ ፕሬዚዳንት ትራምፕን በ2024 እሳቸውን በተመለከተ በሰራው ዘገባ ባለፈው ሳምንት ይቅርታ ጠይቆ ነበር።

ዶናልድ ትራምፕ፤ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት
ዶናልድ ትራምፕ፤ የአሜሪካ ፕሬዚዳንትምስል፦ Daniel Torok/Avalon/Photoshot/picture alliance


የአሜሪካው ፕሬዝዳንትዶናልድ ትራምፕ ከ1 ቢሊዮን  እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የጉዳት ካሳ የሚጠይቅ ክስ ቢቢሲ ላይ  እንሚመሰርቱ  ገለፁ።
ትራምፕ ክሱን በሚቀጥለው ሳምንት ሊመሰርቱ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ቢቢሲ ፕሬዚዳንት ትራምፕን በ2024 እሳቸውን በተመለከተ በሰራው ዘገባ ባለፈው ሳምንት ይቅርታ ጠይቆ ነበር።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድትራምፕ ትናንት አርብ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት «ከአንድ ቢሊዮን እስከ አምስት ቢሊዮን ዶላር ለሚደርስ ገንዘብ እንከሳቸዋለን፣ ምናልባትም በሚቀጥለው ሳምንት  ይህን ማድረግ አለብኝ ብዬ አስባለሁ። እንዲያውም ማጭበርበራቸውን አምነዋል።«ብለዋል።
ትራምፕ የቢቢሲን ጉዳይ ለብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር  እንደሚያነሱ ተናግረዋል። «በሳምንቱ መጨረሻ ልደውልለት ነው። እሱ በእርግጥ ደውሎልኛል።በጉዳዩም በጣም አፍሮአል።»ሲሉም ገልፀዋል።

የቢቢሲ ውዝግብ ምንድን ነው?

በጎርጎሪያኑ 2024የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከመካሄዱ ከቀናት ቀደም ብሎ በተሰራጨው “ፓኖራማ” ዶክመንተሪ  ላይ አሳሳች አርትኦት ምክንያት ቢቢሲ ከትራምፕ ጋር ተጋጭቷል።
ፕሮግራሙ ከትራምፕ ንግግሮች መካከል ከ50 ደቂቃ በላይ ልዩነት ያላቸውን ሁለት ንግግሮች በአንድ ላይ በማጣመር የካፒቶሉን ግርግር እየቀሰቀሰ ነው የሚል ግምት ፈጥሯል።
ዘጋቢ ፊልሙ ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ እፈልጋለሁ ያሉበትን ክፍልም አስወግዶ ነበር።

ቢቢሲ የስም ማጥፋት ክሱ መሰረት የለውም ብሏል

ቢቢሲ ባለፈው ሃሙስ የዩናይትድ ስቴትስፕሬዝዳንት ንግግር ለተቀናበረበት መንገድ ሊቀመንበሩ ሳሚር ሻህ ለዋይት ሀውስ በላኩት ደብዳቤ ይቅርታ ጠይቋል። ቢቢሲ የቪድዮ ክሊፕ የተስተካከለበት መንገድ ከልቡ ቢፀፀትም፣ የስም ማጥፋት መባሉንእንደማይሳማማ  በደብዳቤው ገልጿል።
የቢቢሲ ዋና ዳይሬክተር ቲም ዴቪ እና የዜና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዲቦራ ተርነስ በችግሩ ምክንያት ባለፈው ሳምንት ከስልጣናቸው መልቀቃቸው ይታወሳል።

ፀሐይ ጫኔ
እሸቴ በቀለ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW