ፖለቲካሰሜን አሜሪካ
ትራምፕ በዋሽንግተን ዲሲ ተግባራዊ ያደረጉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 8 2017
ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወንጀል ተስፋፍቷል ባሉበት በዋሽንግተን ዲሲ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ማድረጋቸው ቁጣና ተቃውሞ አስከትሏል። ትራምፕ የአሜሪካን ዋና ከተማ የዋሽንግተን ዲሲ ፖሊስ በፌደራሉ ፖሊስ ስር እንዲሆን መወሰናቸው እና ብሔራዊው ዘብ ከተማይቱ እንዲገባ ማድረጋቸው አሁንም ማወዛገቡ ቀጥሏል።
ብሔራዊው ዘብ ከዚህ ሳምንት ማክሰኞ አንስቶ ወደ ዋና ከተማይቱ መግባት ጀምሯል። ከዚህ ሌላ ትራምፕ በከተማይቱ የተለያዩ ስፍራዎች የሚኖሩ ጎዳና ተዳዳሪዎችንም አነሳለሁ ማለታቸው ሕገ- መንግስታዊ ክርክሮችን አጭሯል። በትራምፕ ውሳኔና ውሳኔው ባስነሳቸው ውዝግቦች ላይ የዋሽንግተን ዲሲውን ዘጋቢያችንን አበበ ፈለቀን ስቲድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
አበበ ፈለቀ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ