ትራምፕ በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው በG20 ጉባኤ ላይ የአሜሪካ ባለስልጣናት እንደማይገኙ ገለፁ።
ቅዳሜ፣ ጥቅምት 29 2018
ትራምፕበደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው በG20 ጉባኤ ላይ የአሜሪካ ባለስልጣናት እንደማይገኙ ገለፁ።ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደገለፁት ፤በደቡብ አፍሪካ በG20 ስብሰባ የአሜሪካ ባለስልጣናት የማይሳተፉት ፤ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ስርዓታዊ በሆነ መንገድ ነጭ የሀገሪቱ ዜጎች “ተገደለዋል እና ተጨፍጭፈዋል” በሚል ቀደም ሲል ያቀረቡትን ክስ ለማጠናከር ነው።ትራምፕ ባለፈው መስከረም ወር በእርሳቸው ምትክ ምክትል
ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ወደ ስብሰባው እንደሚጓዙ አስታውቀው ነበር።ነገር ግን አሁን የዩኤስ ተወካዮች ሙሉ በሙሉ አይሳተፉም ብለዋል ።"G20 በደቡብ አፍሪካ መካሄዱ በጣም አሳፋሪ ነው" ሲሉ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በሚባለው የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል። እነዚህ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች እስካሉ ድረስ የትኛውም የአሜሪካ መንግስት ባለስልጣን አይገኝም። ሲሉም አክለዋል።ትራምፕ እንዳሉት የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያዎቹ አውሮፓውያን ሰፋሪ የሆኑት አፍሪካንስ የሚባሉት ነጭ ደቡብ አፍሪቃውያን ገበሬዎች "እየተገደሉ እና እየታረዱ ነው። መሬታቸውና እርሻቸው በህገ ወጥ መንገድ እየተነጠቀ ነው።"ትራምፕ ፤ዩናይትድ ስቴትስ የ2026 G20 ስብሰባን ለማስተናገድ በጉጉት እየጠበቀች መሆንንም ጨምረው ተናግረዋል።
የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የትራምፕን አስተያየት "አሳዛኝ" በማለት በጎርጎሪያኑ ከህዳር 22 እስከ 23 የሚካሄደውን ጉባኤ በተሳካ መንገድ ለማስተናገድ በጉጉት እየጠበቅን መሆኑን ገልጿል።
የደቡብ አፍሪቃ መንግስት አፍሪካነርስን ብቸኛ ነጭ ቡድን ብሎ መፈረጅ ታሪካዊ ነው።በተጨማሪም ይህ ማህበረሰብ ለስደት ይዳረጋል የሚለው አባባል እውነተኛ እና የተረጋገጠ አይደለም"ብሏል በመግለጫው።ፕሪቶሪያ ለምታስተናግደው የG20 ስብሰባ “አንድነት፣ እኩልነት፣ ዘላቂነት” የሚል መሪ ቃልን መርጣለች። ያም ሆኖ ዋሽንግተንን ጨምሮ አንዳንድ ተቃውሞ ገጥሟታል።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳለው "የደቡብ አፍሪካ ትኩረት በአዎንታዊ ዓለም አቀፍ አስተዋፅዖዎች ላይ ይቆያል" ብሏል።ሲል የዘገበው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ነው።
ፀሀይ ጫኔ
ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሄር