1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ትኩረትን የሚሻው የካንሰር በሽታ

ሐና ደምሴ
ቅዳሜ፣ የካቲት 1 2017

የካንሰር ህመምተኞች መካከል የህክምና አገልግሎት የሚያገኙት 15,000 እንደማይሞሉ መረጃዎች ያመላክታሉ። አሁን በኢትዮጵያ ባለው መረጃ መሰርት የጡት ካንሰር በሽታ ከፍተኛ ቁጥር የያዘ ሲሆን የማህፅንና የአንጀት ካንሰር በሽታ በርካቶችን እያጠቃ እንደሆነ ተነግሯል ።

ትኩረትን የሚሻው የካንሰር በሽታ
ትኩረትን የሚሻው የካንሰር በሽታምስል፦ crytallight/Depositphotos/IMAGO

ትኩረትን የሚሻው የካንሰር በሽታ

This browser does not support the audio element.

የዓለም ካንሰር ቀን በየዓመቱ በጎርጎሪዮሳዊው አቆጣጠር  የካቲት ወር መግቢያ ላይ ይታሰባል። የዘንድሮው የካንሰር ቀን  ሲታሰብ  «በልዪነት አንድ መሆን ታማሚዎችን ማዕከል ያደረገ ህክምና» በሚል መሪ ቃል ለሚቀጥሉት ሁለት አመት ይታሰባል።   
በኢትዮጵያ በየአመቱ 80,000 ያሀል አዳዲስ የካንሰር ህመሟን  ይመዘገባሉ። በሆስፒታሎች ለሀክምና የሚመጡ  ህመምተኞች ብቻ ያካተተ በመሆኑ ነው እንጂ  ይህ ቁጥር ከዚህም ብላይ ይሆናል ተብሎ ይገመታል ። 
ከነዚህ  አዳዲስ ከሚመዘገቡት የካንሰር ህመምተኞች መካከል የህክምና አገልግሎት የሚያገኙት 15,000 እንደማይሞሉ መረጃዎች ያመላክታሉ።  አሁን በኢትዮጵያ  ባለው መረጃ መሰርት  የጡት ካንሰር በሽታ ከፍተኛ ቁጥር የያዘ  ሲሆን  የማህፅንና የአንጀት ካንሰር በሽታ  በርካቶችን እያጠቃ እንደሆነ ተነግሯል ።
የካንሰር በሽታ እንዴት እና በምን ሁኔታ እንደሚመጣ ማውቅ ባይቻልም  የተውሰኑትን የካንሰር አይነቶች ቅድመ ምርምራ በማድረግ መከላከል እና ጥንቃቄ ማድረግ ይቻላል ሲሉ ለ DW የተናገሩት የካንሰር ታካሚዎችን ማእከል ያደረገ ሆፕ ኦን ኮሎጂ የተሰኛውን የህክምና ማእከል ከ ባልደርቦቻቸው ጋር የመሰረቱት ዶክተር ሙኒር  አወል ናቸው።  «ህክምናውን ማግኘት ፈተና ነው እንዲያም ሆኖ ሲገኘ ታካሚውን ብቻ ሳይሆን ቤተሰቡን ሁሉ ይጎዳል። አቅምን ይፈትናል» በማለትም ያክላሉ።
ምንም እንኳን  የካንሰር በሽታ እና ህክምናው እንደ የሰው ቢለያይም የካንሰር ታካሚዎቸን አንድ የሚያደርጋቸው  የየራሳቸው የሆነ ታሪክ አላቸው እና  ህክምናውን  ሳይፈሩ የመዳን ተስፋ ይዘው ከህመም አና ከስቃዪ ተሻግረው የዳኑት ሰዎች እየተገኛኙ ይወያያሉ እርስ በርስ ይበረታታሉ  ለሌላው ጉልበት ይሆናሉ።
ከቅርብ ግዜ ወዲህ በተደጋጋሚ  በጣም ጤናማ በሚመስሉ እና ወጣት ሰዎች ላይ  ተከስቶ  የምንሰማቸው የካንሰር በሽታ አይነቶች መብዛት  እና መደጋገም ከምን የመጣ ነው? ስል ላቀረብኩላቸው ጥያቂ  ዶክተር ሙር ሲመልሱ
«በተላላፊ በሽታ የሚሞተውን ሀዝብ ቁጥር መቆጣጣር ያልቻለችው ኢትዮጵያ አሁን ባለው  የካንሰር ህክምና መሰጫ ማእከልእና  ሆሰፒታሎ‍ች እጥረት ፤ በዘርፉ የሰለጠኑ የህክምና ባለሙያዎች አለመኖር፤  የህከምና ወጭው ከአብዛኛው የማህበረሰብ አቅም በላይ መሆን እና ማህበረሰቡ ስለበሽታው ትክከለኛ ግነዛቤ አለመኖር ታክሎበት አፋጣኝ ትኩረት ካልተሰጠበት አሳሳቢ ይሆናል» ብለዋል ።
ሃና ደምሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር


 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW