1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኬንያ ማታቱ ሚኒባሶች

ቅዳሜ፣ መጋቢት 30 2015

የፋይናንስ ባለሙያዎች እንደሚያምኑት በናይጄሪያ የገንዘብ ቀውሱ በአፍሪካ ታላቅ ኢኮኖሚ በምታንቀሳቅሰው ናይጀሪያን 20 ትሪልዮን ናይራ ወይም ወደ 40 ቢልዮን ዶላር አካባቢ ዋጋ አስክፍሎአታል።

Nigeria vor Wahlen | Mangel an Bargeld
ምስል፦ Ben Curtis/AP/picture alliance

ትኩረት በአፍሪቃ

This browser does not support the audio element.

ጤና ይስጥልን ውድ የትኩረት በአፍሪቃ ዝግጅት ታዳሚዎች። በዛሬው ዝግጅታችን በሁለት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እናተኩራለን። በኬንያ የሚኒባስ ረዳቶች ተሳፋሪን ለመሳብ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የራሳቸውንና የተሳፋሪዎችን ደህንነት አደጋ ላይ መጣሉን እንዲሁም በአፍሪቃ የሥራ እጥነት ችግር ላይ የሚያጠነጥኑ ዝግጅቶች እናቀርባለን።
በተለያዩ ሐገሮች የሚገኙ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቢሶችና ሚኒባሶች ተሳፋሪን ለመሳብ የሚጠቀሙት ዘዴ ይለያያል። እንደልዩነቱ ሁሉ ጥቅምና ጉዳቱም የተለያየ ነው። በኬንያ ያለው ግን ለየት ሳይል አይቀርም። በኬንያ በሕዝብ ማመላለሻ አውቶቢሶችና ሚኒባሶች በተለይም እነሱ «ማታታ» ብለው የሚጠሯቸው ሚኒባሶች የሚሰሩ ረዳቶች ደንበኛቸውን ለመሳብ የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሱዎችን ያደርጋሉ። የበሩን የላይኛው ክፍል በሁለት እጃቸው በመያዝ ሁለት እግራቸውን ከመኪና ውጭ እያንጠላጠሉ  ሽቅብ ወደላይኛው የመኪናው ውጫዊ ጣራ እያጠፉ፤ እንዲያም ሲል ጎንለጎን ከሚተላለፈው ተመሳሳይ መኪና በእግራቸው እየነኩ እራሳቸውንና ተሳፋሪውን ለአደጋ በሚያጋልጥ መልኩ ሲንቀሳቀሱ ማየት የዘወትር ተግባር ሆኗል። መቼስ የነሱስ እራሳቸው ያመጡት ተብሎ ቢታለፍ እንኳ ተሳፋሪው መኪናው ሳይቆም እንዲወርድ የሚደረግበት ሁኔታ ግን ብዙዎቹን እያነጋገረ ነው።
ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው ከሚሠሬ መካከል ወጣት ማዮቲ በአንዱ ነው። ለዚህ አደገኛ ሥራውም በአንድ ጉዞ አንድ ዶላር ይከፈለዋል።
"የማደርገው ነገር ምንም አደጋ አያስከትልብኝም ፤ ምክንያቱም ለረጅም ጊዜ ሠርቼዋለሁ ፤ ደግሞም ሁሌ የምጠቀምበት ነው ። ይህ ልማድ ልክ እንደ ማርሻል አርት ነው ፤ ልምምድ ትክክለኛ ያደርጋል ይባል የለ ። ማታቱ ላይ ይህን ሳደርግ በአሁን ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት መንገደኞችን አሳፈራለሁ ። እንዲህ በማድረግ የስድስት ዓመታት የሥራ ልምድ አካብቻለሁ "።
ወጣቱ ማዮቲ ይህን ይበል እንጂ ተግባሩን ግን ብዙዎችን እያሳሰበ ነው። ይህ ለአደጋ የሚያጋልጥ ድርጊታቸውን ካሳሰባት አንዷ ተማሪ አን ቪታ ትገኝበታለች።

"ብዙውን ጊዜ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር እንደሆነ ይሰማኛል ፤ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉት መኪናው እየተንቀሳቀሰ በመንጠላጠላቸው  ነው፤ ምክንያቱም አንድ ሰው በሌላ መኪና ተገጭ ሕይወቱን ሊያጣ ይችላል ።»

ምስል፦ Getty Images/AFP/T. Karumba
ምስል፦ Getty Images/AFP/T. Karumba

ኬንያ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ ከሚደርስባቸው አገሮች አንዷ ናት። የሚወጡ ወቅታዊ መረጃዎች አዝማሚያው እሻቀበ መሆኑን ሲያመላክቱ ደግሞ ሁኔታው አስጨናቂ ያደርገዋል። የየመጓጓዣና የመንገድ ደህንነት ባለሙያው ኦዳምቦ ድርጊቱ ዘግናኝ እልቂት ሊያስከትል እንደሚችል ያስጠነቅቃል።

"ማታቱዎች የሚሰሩ ረዳቶች  መኪናው በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ተንጠልጥለው መንቀሳቀሳቸው በራሳቸው ብቻ ሳይሆን በመንገድ ተጠቃሚዎች ላይም ጭምር ከፍተኛ አደጋ ሊያስከትል ይችላል ። በሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎች ላይም ተጨማሪ ወጪ ነው ። እንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች ከባድ ቅጣቶች ሊጣልባቸው ይገባል ። "

በናይጄሪያ የተፈጠረው የጥሬ ገንዘብ እጥረት

በናይጄሪያ የታየው የጥሬ ገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ የሃገሪቱ  ማዕከላዊ ባንክ ንግድ  ባንኮች ለደንበኞቻቸው  የሚያሰራጩትን  ጥሬ ገንዘብ በእጥፍ እንዲጨምር አድርጓል። የባንኩ ባለስልጣናት  በሃገሪቱ ያሉ የንግድ ባንኮች በሙሉ የገንዘብ መክፈያ ማሽኖቻቸው ማለትም ATM ገንዘብ እንዲጭኑና በሳምንቱ የዕረፍት ጊዚያትም ሥራ ላይ እንዲሆኑ እንዲያደርጉ መመሪያ ሰጥተዋል። ይህም በአፍሪካ ታላቅ ኢኮኖሚ የምታንቀሳቅሰው ናይጀሪያ የገንዘብ ውድቀት እንዳያጋጥማት በማሰብ ነው ተብብሏል። በተጨማሪም አሮጌ የናይራ ብሮች እስከ ዓመቱ መጨረሻ እንዲንቀሳቀሱ አዘዋል።
የናይጀሪያ ማዕከላዊ ባንክ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር እስከ የካቲት 2023 ዓ.ም የሃገሪቱ የ200፣ 500፣እና የ1000 የብር ኖቶች እንዲቀየሩ የጊዜ ገደብ ካስቀመጠ ወዲህ በአገሪቱ ከአንድ ዓመት በላይ በጥሬ ብር እጥረት ተከስቷል። 

ደምበኞች እስከአሁን ጥሬ ብር እያገኙ አደለም

አዲሱ የብር ኖት ማሰራጨት ያስፈለገበት ምክንያት ከባንክ አገልግሎት ውጪ ያለውን ትርፍ ገንዘብ ለማጽዳት ፣ ሙስናን ለመከላከልና ለአማጽያን ሽፍቶችና ጠላፊዎች የሚከፈለውን የቤዛ ክፍያ ለማስወገድ ታስቦ የተዘጋጀ ነበር ። ሆኖም ግን የሃገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ እንዲህ አይነት ጥረት ቢያደርግም አንዳንድ ናይጄሪያውያን ከባንክ ዘርፉ እንዲሸሹ አድርጓቸዋል፤ በደንብ ያልተተገበረው የናይራ ፖሊሲ የሥርአቱን ብቃት ማነስን አጋልጧል።
በአለፈው ሳምንት የሃገሪቱ የሰራተኞች ምክር ቤት በሃገሪቱ የተከሰተውን የገንዘብ እጥረት በማስመልከት አድማ እንደሚጠራ ዝቷል። ይሁንና አድማው በሁለት ሳምንታት ተገፍቷል። የኮንግረሱ ፕረዚደንት ጆ አጃሮ ድርጅታቸው ለናይጄርያውያን እንዴት ጥሬ ብር ተደራሽ እየሆነ እንደሆነ ክትትል እያደረገ እንደሆነ ተናግሯል። ይሁንና እንደ ሳምሶን አደቦ ያሉ በርካታ ደምበኞች ሁኔታው እንዲሁ ቀላል አይደለም። ሳምሶን በሰሜን ናይጄሪያ በሚገኝ አንድ ባንክ አገልግሎት ለማግኘት ሲጠባበበቅ በነበረበት ወቅት ለDW ተከታዩን አስተያየት ሰጥቷል።
 
`` ሕዝቡ ጥሬ ገንዘብ ለማግኘት እየታገለ በመሆኑ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተሰብስቦ ታያለህ።በእውነቱ ወዚህ በርካታ ጊዜ ተመላልሻለሁ። ይሁንና የፈለግኩትን ማግኘት አልቻልኩም። እንደማስበው በድፍን ናይጄሪያ ወደሚገኙ ባንኮች ብትሄድ እነሱ ጥሬ ገንዘብ አለ ቢሉም በርካታ ሕዝብ ተሰብስቦ ወረፋ ሲጠብቅ ታያለህ``
የፋይናንስ ባለሙያዎች እንደሚያምኑት የገንዘብ ቀውሱ በአፍሪካ ታላቅ ኢኮኖሚ በምታንቀሳቅሰው ናይጀሪያን 20 ትሪልዮን ናይራ ወይም ወደ 40 ቢልዮን ዶላር አካባቢ  ዋጋ አስክፍሎአታል። በተጨማሪም ደንበኞች ገንዘባቸውን በባንክ ከማስቀመጥ እየሸሹ ስለሆነ የባንኩ ዘርፍ እንዳይወድቅ ስጋትን ፈጥሯል። ብሔራዊ ባንኩ ግን ደምበኞች በትእግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል።
ምንም እንኳን የንግድ ባንኮች አዲሱን የብር ኖት በATM ማለትም በመክፈያ ማሽኖቻቸው እንዲጭኑ ቢታዘዙም አንዳንድ ደንበኞች ለDW እንዳሉት ሁሉም ግን ተገዢ አደሉም።

`` መንግስት አሁን በናይጄሪያ ከሚንቀሳቀሱ የንግድ ተቋማት 75 በመቶው አነስተኛ መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች መሆናቸውን የተገነዘበ ይመስላል። እነዚህ ደግሞ ንግዳቸው በጥሬ ገንዘብ ክፍያ ላይ የተመሰረተ ነው። ስለሆነም  እነዚህ ኢንተርፕራይዞች እንደ ሞባይል የባንክ አገልግሎት፣ ኢንተርኔት ኢንተርኔት የባንክ አገልግሎት እና የመሳሰሉ ሌሎች የመክፈያ ዘዴዎችም ጥቅም ላይ ሊያውሉ ይመከራል።``

ምስል፦ Pius Utomi Ekpei/AFP

እንደ ፋጡማ አቡበክሪ ከሆነ የሃገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ ለደካማ የገንዘብ ለውጥ ስርዓት ሃላፊነት ሊወስድ ይገባል። በተለይ መደበኛ ያልሆኑ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ክፉኛ ጎድቷልና።

`` ሲጀመር የናይጄሪያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱን ገንዘብ የማስቀየሪያ የጊዜ ገደብ ሲያስቀምጥ ሕዝቡ የማይቻል ነው ብሎ ስላሰበ ምንም እርምጃ አልወሰደም። በገጠር የሚኖሩ አብዛኛዎቹ ሰዎች ግብይት ለማድረግ አስቸጋሪ ሆኖባቸው ነበረ። እናም የሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጣልቃ እንዲገባ ያደረጉ ብዙ ቅሬታዎችን ፈጥሯል። አሁን የገንዘብ መቀየሪያ ጊዜ በመራዘሙ ሕዝቡ ትንሽ ፈታ ያለ ቢሆንም ፖሊሲው ግን ጤናማ አደለም።``
አሁን ያለውን የኢኮኖሚ ሁኔታን ለማረጋጋት የናይጄሪያ ማዕከላዊ ባንክ፤ ደንበኞች ክፍያን ለመፈጸም የኢንተርኔት የባንክ አገልግሎት  በአማራጭነት እንዲጠቀሙ እናበረታታለን ብሏል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW