1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትውልደ-ኢትዮጵያዊው የጀርመን የምርጫ አስፈጻሚ

ሐሙስ፣ መስከረም 13 2014

ከዛሬ ዐርባ አምስት ዓመት በፊት ለትምሕርት ወደ ጀርመን ሀገር እንደመጡ የሚናገሩት አቶ እሸቱ ወንዳፍራሽ ምዕራብ ጀርመን የምትገኘው የአኸን ከተማ የምርጫ አስፈጻሚ ናቸው። በጀርመን አገር አቀፍ ምርጫ ፣በአካባቢያዊና በአውሮጳ ኅብረት ምርጫዎች በተለያዩ ጊዜያት በምርጫ አስፈጻሚነት አገልግለዋል።

Deutschland I Eshetu Wendafirash, äthiopischer Wahlbeobachter bei der Wahl in Aachen
ምስል Hirut Melesse/DW

በስምንት የተለያዩ ምርጫዎች በኃላፊነት ሠርተዋል

This browser does not support the audio element.

ከዛሬ ዐርባ አምስት ዓመት በፊት ለትምሕርት ወደ ጀርመን ሀገር እንደመጡ የሚናገሩት አቶ እሸቱ ወንዳፍራሽ ምዕራብ ጀርመን የምትገኘው የአኸን ከተማ የምርጫ አስፈጻሚ ናቸው። በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ጀርመን ያጠናቀቁት አቶ እሸቱ፦ በጀርመን አገር አቀፍ ምርጫ ፣በአካባቢያዊና በአውሮጳ ኅብረት ምርጫዎች በተለያዩ ጊዜያት በምርጫ አስፈጻሚነት አገልግለዋል። የፊታችን እሁድ በሚካሄደው ምርጫም በከተማቸው በአኽን የምርጫ አስፈጻሚ ናቸው። አቶ እሸቱ የዘንድሮውን ምርጫ ጨምሮ በስምንት የተለያዩ ምርጫዎች በዚሁ ኃላፊነት ሠርተዋል። በጀርመን የምርጫ አስፈጻሚ አመራረጥ፣ ኃላፊነት እና የድምፅ አሰጣጡ ሂደት ምን እንደሚመስል ኂሩት መለሰ ከዶቼቬለ የጋዜጠኞች ቡድን ጋር አኽን በነበራት ቆይታ አቶ እሸቱን አነጋግራቸዋለች።  

ኂሩት መለሰ


እሸቴ በቀለ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW