1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ «ደሚህት» መሪ ወቅታዊ ሁኔታ

ዓርብ፣ መስከረም 7 2008

ትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ «ደሚህት»ተብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ከተዋጊዎቻቸዉ ጋር ከጥቂት ቀናት በፊት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋአል።

Karte Äthiopien englisch

[No title]

This browser does not support the audio element.



የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣዉ መግለጫ ፣የኢትዮጵያ መንግስት የደሕንነት አካላት ከድተዉ ከገቡት ከደሚህት መሪ ጋር ዓመት ከዘለቀ ምስጢራዊ ድርድር በኋላ ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ መደረጉን መግለፁ ይታወቃል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር አዳማ ናቸው የተባሉትን የ(ደሚህት)ን መሪ አቶ ሞላ አስገዶምን ለማግኘት አዳማ ሄዶ ሊያገኛቸው አለመቻሉን ገልፆልናል።

በሌላ በኩል «የአርበኞች ግንቦት ሰባት» አመራር አባልና የድርጅቱ ቃል አቀባይ ዶክተር ታደሰ ብሩ ከዶይቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራስያዊ ንቅናቄ በምህፃሩ «ደሚህት» መሪና ጥቂት አባላቱ መክዳት ቀሪዉን ከፍተኛ ኃይል ያጠናክራል እንጂ አያዳክምም አሉ። ዶክተር ታደሰ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ የደህንት መሪ ኢትዮጵያ ይዘው ገቡ የሚባለው ተዋጊ ቁጥር ቡድኑ ካለው ሠራዊት ቁጥር ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ነው ብለዋል ።


ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

መክብብ ሸዋ

አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW