የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም ማሳሰቢያ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 29 2016
የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያ ፖርላማም ይሁን ሌሎች ምክርቤቶች ውክልና ስለሌለው የተለያዩ ችግሮች መፍትሔ እንዳያገኙ አድርጎ እንዳለ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ። በኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመቐለ ቅርንጫፍ ፅሕፈት ቤት በኢትዮጵያ ፖርላማ ይሁን ፌደሬሽን ምክርቤት የትግራይ ውክልና እንዲኖር ጥሪ አቅርቧል። ጦርነቱ ተከትሎ ትግራይ በኢትዮጵያ ፖርላማ ይሁን ፌደሬሽን ምክርቤት የነበራት ውክልና አጥታለች። ይህን ተከትሎ የትግራይ ህዝብ መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎች፣ ፍላጎቶች ይሁኑ ቅሬታዎች በሀገሪቱ የበላይ የሕግ አውጪ አካል እየተንፀባረቁ አይደለም ተብሏል።
የፌደሬሽኑ አባልና መስራች ትግራይ፥ አስቀድሞ የነበረው መካረር እና ጦርነቱ ተከትሎ፥ ላለፉት ከሶስት በላይ ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት እና በፌደሬሽን ምክርቤት ሕጋዊ ውክልና የሌላት ሆና ትገኛለች። ትግራይ በኢትዮጵያ ፖርላማ የነበራት 38 መቀመጫ እንዲሁም በፌደሬሽን ምክርቤት የነበራት ውክልና አሁን ላይ ባለመኖሩ፥ የህዝቡ ጥያቄዎች፣ በደሎች፣ ቅሬታዎች እንዲሁም የመብት ጥያቄዎች በሀገሪቱ የበላይ ሕግ አውጪ አካላ በቀጥታ ቀርቦ መወያያ አጀንዳ እንዳይሆን እንዳደረገው የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ይገልፃሉ።እንባ ጠባቂ በትግራይ ክልል ከሦስት ሺህ በላይ የፖሊስ አባላት ከሥራ ታግደዋል አለ
ከ2002 ዓመተ ምህረት እስከ 2012 ዓመተምህረት መጨረሻ ከትግራይ ክልል ተመርጠው በኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል ሆነው የቆዩት ያነጋገርናቸው የቀድሞ የፓርላማ አባሉ አቶ ገብረእግዚአብሔር አርአያ፥ በዚህ አንገብጋቢ ወቅት ትግራይ በኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ይሁን የፌደሬሽን ምክርቤት ውክልና ሳይኖራት መቅረቷ በውሳኔዎች ላይ ተሳትፎ የሚያሳጣት እንዲሁም የህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄዎች አጀንዳ እንዳይሆኑ የሚያደርግ ብለው ይገልፁታል። አቶ ገብረእግዚአብሔር "በምክርቤቶቹ የትግራይ ውክልና ባለመኖሩ የትግራይ ህዝብ ድምፅ የሚሰማበት ሁኔታ ዝግ ሆኖ ነው ያለው ማለት ነው። ጉዳይህ ሌሎች እንዳያነሱ አትጠብቅም። ህዝቡ ድምፁ የሚያሰማበት ቀጥተኛ ዕድል አሁን ላይ የለዉም። የትግራይ ህዝብ ድምፅ ሊሰማበት የሚችልባቸው የፌደሬሽን እና የምክርቤት ውክልና ተነጥቆ ነው ያለው" ይላሉ።የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጥሪ
ከዚህ በተጨማሪ የቀድሞ ፓርላማ አባሉ በፌደሬሽኑ ውክልና አለመኖር የህዝብ መብት መግፈፍ የመሆኑ ይገልፃሉ። የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም በበኩሉ በኢትዮጵያ የተለያዩ ምክርቤቶች የትግራይ ህዝብ ውክልና ባለመኖሩ አስተዳደራዊ ችግሮቹ ምላሽ እንዳያገኙ እንቅፋት ሆኖ እንዳለ ይገልፃል። ለዶቼቬለ የተናገሩት በኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የመቐለ ቅርንጫፍ ፅሕፈት ቤት እምባ ጠባቂ አቶ ፀሐየ እምባየ በሀገራዊ ምክርቤቶች የትግራይ ውክልና እንዲረጋገጥ ተቋማቸው ጥሪ እንደሚያቀርብ ይናገራሉ።
በኢትዮጵያ ፓርላማ እና የፌደሬሽን ምክርቤት የትግራይ ውክልና እንዲኖር፥ የሰላማ ስምምነቱ በአፋጣኝ ተተግብሮ፣ በትግራይ የተመረጠ መንግስት የሚቋቋምበት ሁኔታ ሊመቻች ይገባል የሚሉት የቀድሞ የፓርላማ አባሉ አቶ ገብረእግዚአብሔር አርአያ፥ ለዚህ የሚያበቁ ተግባራት በፌደራል መንግስቱ እና በክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ሊተገበሩ እንደሚገባ ይጠቅሳሉ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዳሰሳአቶ ገብረእግዚአብሔር "አፋጣኝ በሆነ መንገድ የራሳችን መንግስት ቶሎ መርጠን ወደ መደበኛ ስርዓት የምንገባበት ሁኔታ ሊመቻች፣ ተጠያቂነት የሚሰፍንበት ሁኔታ ሊፈጠር፣ በፌደራል መዋቅሩ የእኛ ጉዳይ ሌሎች ሊወሱኑልን ሳይሆን፥ እኛው ራሳችን የምንወስንበት ስርዓት ሊፈጠር የሚችልበት አግባብ እንዲኖር ይገባል። ይህ ማስተካከል የትግራይ ህዝብ ካለው ችግር ሊወጣ፣ ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሚያገኝበት፣ ድምፁ የሚሰማበት ሁኔታ የሚያስተካክል ነው" ብለዋል።
በዚህ አጀንዳ ዙርያ ከኢትዮጵያ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ክልል ውስጥም የነበረው የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በፕሪቶርያው ውል መሰረት የፈረሰ ሲሆን፥ ይህ ክፍተት የሚተካ አልያም በትግራይ ያሉ የተለያዩ አመለካከቶች የሚያንፀባርቅ ይሆናል የተባለ አዲስ ካውንስል ለማቋቋም የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር እየሰራ መሆኑ ይገልፃል።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ