1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ተፈናቃዮች ቅሬታ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 22 2016

የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ግጭት የማቆም ስምምነት ከተፈራረሙ አንድ ዓመት ቢደፍኑም በጦርነቱ ወቅት ከትግራይ ክልል የተፈናቃሉ ነዋሪዎች ወደየቀያቸዉ አለመመለሳቸዉ እንዳሳሰባቸዉ እየተናገሩ ነዉ። የተፈናቃዮቹ እንደሚሉት ስምምነቱ ሲፈረም ወደየቀያችን እንመለሳል የሚል ተስፋ አሳድረን ነበር።

የተፈናቃዮች መጠለያ ጣንያ በትግራይ
የተፈናቃዮች መጠለያ ጣንያ በትግራይ ምስል Million Haileselassie/DW

ትግራይ ዉስጥ አሁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በየመጠለያ ጣቢያዉ እንደሰፈሩ ነዉ

This browser does not support the audio element.

  
የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ግጭት የማቆም ስምምነት ከተፈራረሙ አንድ ዓመት ቢደፍኑም በጦርነቱ ወቅት ከትግራይ ክልል የተፈናቃሉ ነዋሪዎች ወደየቀያቸዉ አለመመለሳቸዉ እንዳሳሰባቸዉ እየተናገሩ ነዉ።የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ሐይለ ስላሳ ያነጋገራቸዉ ተፈናቃዮች እንደሚሉት ስምምነቱ ሲፈረም ወደየቀያችን እንመለሳል የሚል ተስፋ አሳድረዉ ነዉ።ይሁንና የትግራይ ዉስጥ አሁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በየመጠለያ ጣቢያዉ እንደሰፈሩ ነዉ። 

በጦርነቱ ምክንያት ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በትግራይ የተለያዩ መጠልያዎች ያሉ ተፈናቃዮች፥ ከሰላም ስምምነቱ አንድ ዓመት በኃላም ቢሆን ወደ ቦታቸው አለመመለሳቸው ቅሬታ ፈጥሮባቸዋል። ከ15 ሺህ በላይ በአብዛኛው ከምዕራብ ትግራይ ዞን የተፈናቀሉ ዜጎች ተጠልለውበት በሚገኙ መቐለ ሰብዓ ካሬ መጠልያ ጣብያ ያነጋገርናቸው ተፈናቃዮች፥ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ተኩስ ከማቆም በዘለለ፣ ነገሮች ወደቅድመ ጦርነት ሁኔታ ሊመልስ ተስፋ ጥለዉበት የነበረ ቢሆንም የተፈፀመ አንዳች ነገር የለም ይላሉ።ዓብይዓዲ የሚገኙ ተፈናቃዮች ስሞታ
አቶ አብርሃ ገብረዮሐንስ ከያፈናቀላቸው ጦርነት ጅማሮ በፊት በሰቲት ሑመራ ይኖሩ የነበሩ አርሶአደር ናቸው። ከሶስት ዓመት በፊት ጦርነቱ ሲቀሰቀስ፥ ከነቤተሰባቸው ቤታቸው ጥለው ተፈናቀሉ። አሁን ላይ በመቐለ የተፈናቃዮች መጠልያ የሚኖሩት አቶ አብርሃ ፥ ተስፋ ያደረጉበት የሰላም ስምምነት ወደ ቀዩአቸው አልመለሳቸውም። የስምንት የቤተሰብ አባላት መሪዋ እናት ወይዘሮ ብርሃን ተካ ኑሮአቸው በተፈናቃዮች መጠልያ ካደረጉ ሶስት ዓመት ሊሞላ ጥቂት ሳምንታት ቀርተዋል ይላሉ። ወይዘሮዋ ከስምምነቱ አንድ ዓመት በኃላም ቢሆን ወደቀየአችን አለመመለሳችን ተስፋ እንድንቆርጥ አድርጎናል ባይ ናቸው። ወይዘሮ ብርሃን ጨምረዉም "እኔ ራሱ ሶስት አራት ሰራተኞች ነበሩኝ። ሰርቼ ነበር የምኖረው። አሁን ተፈናቃይ ሆኞ እርዳታ እየጠበቅኩኝ ነው። ሰላም ሆነ ሲባል ተስፋ ነበረኝ። የተቀየረ ነገር ግን የለም። አሁንም ግን የምለው እርዳታ አምጡልን ሳይሆን፥ ዘላቂ ወደ ቦታችን መልሱን ነው። ከረድኤት ይልቅ ወደ ቦታየ መመለስ እፈልጋለሁ" ይላሉየትግራይ ሴት ተፈናቃዮች

የትግራይ ጦርነት ተጎጅዎችምስል Million Haileselassie/DW

ያነጋገርናቸው ተፈናቃዮች እስካሁን ወደቀዬአቸው ላለመመለሳቸው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር እና የፌደራል መንግስቱን ተወቃሽ ያደርጋሉ። ከምዕራብ ትግራይ የተፈናቀሉት አቶ ኪዱ አረጋይ"ያለምንም መፍትሔ አዲስአበባ ሄዶ መሰብሰብ፣ ደርሶ መመለስ ለትግራይ ህዝብ ትርጉም የለውም። ወይ እርዳታ ተገኝቶ ረሃቡ በቀነሰልን፣ ወይ ወደቀዬችን ተመልሰን እንደ ድሮአችን ጥረን ግረን በበላን ወይ ሌላ መፍትሔ ቢሰጠን ጥሩ ነበር። በቃ ግን ተዘንግተናል። መንግስት ረስቶናል። ለዚህ ነው ድርድር ተደረገ፣ የሰላም ስምምነት ተፈረመ የተባለው ? ለመናገሩም አስቸጋሪ ነው" ይላሉ።የሱዳን ጦርነት መዘዝ ለኢትዮጵያዉያን ስደተኞች

ሌላው ተፈናቃይ አቶ ክፍለየሱስ መስፍን ፥ እኛም ኢትዮጵያውያን ነን፣ የኢትዮጵያ መንግስት መፍትሔ ይስጠን ይላሉ። በዚሁ የተፈናቃዮች ቅሬታ ዙርያ ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግሰት እና ከትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለግዜው አልተሳካም። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ተፈናቃዮች ወደቀያቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ሐላፊነቱ ይወጣ ሲል ሲገልፅ ቆይቷል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 

ነጋሽ መሐመድ 

ኂሩት መለሰ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW