1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትግራይ ከኤኮኖሚ ማሻሻያው በኋላ እንደንምን ሰነበተች ?

ሐሙስ፣ ነሐሴ 9 2016

በውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ከተደረገ በኃላ በመቐለ በሸቀጦች እና አገልግሎቶች ላይ የተወሰነ የተባለ የዋጋ ጭማሪ እየታየ መሆኑ ነጋዴዎች እና ሸማቾች ይገልፃሉ። የአስተዳደር አካላት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌላው የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ነጋዴዎች እና አገልግሎት ሰጪዎች እርምጃ እየወሰዱ መሆኑ አስታውቀዋል።

Äthiopien | Markt in Mekelle
ምስል Million Haileslasse/DW

ትግራይ ክልል ዉስጥ ጎላ ያለ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል

This browser does not support the audio element.

በውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ከተደረገ በኃላ በመቐለ በሸቀጦች እና አገልግሎቶች ላይ የተወሰነ የተባለ የዋጋ ጭማሪ እየታየ መሆኑ ነጋዴዎች እና ሸማቾች ይገልፃሉ። የአስተዳደር አካላት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌላው የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ነጋዴዎች እና አገልግሎት ሰጪዎች እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ ያለው ግጭት፤ የኢኮኖሚ ማሻሻያው አተገባበር ስጋት

ተዘዋውረን በተመለከትናቸው የመቐለ የተለያዩ የገበያ ስፍራዎች እንደታዘብነው እና ሸማቾች እና ነጋዴዎች እንደገለፁልን፥ በተለይም ከውጭ በሚገቡ የምግብ ነክ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚታይ ሲሆን፥ ይሁንና እጅግ በጣም ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቶበት ከነበረው የዛሬ ሁለት ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በሂደት የተወሰነ ቅናሽ እየታየ መሆኑ ይነገራል። የጤፍ ዋጋ ለኩንታል ከ14 ሺህ ብር እስከ 11 ሺህ ብር እንደየ ደረጃው፣ ስንዴ 7 ሺህ ለኩንታል፣ የዘይት ዋጋ ባለ አምስት ሊትር ከ1 ሺህ እስከ 1 ሺህ አንድ መቶ በዛሬ ገበያ ሲሸጡ ታዝበናል። ያነጋገርናቸው ነጋዴዎች እንደሚሉት፥ በውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ከተደረገ በኃላ በተለያዩ ሸቀጦች የተወሰነ ጭማሪ ቢኖርም፥ በቅርቡ ግን ገበያው እየተረጋጋ መሆኑ ይናገራሉ።

የመቐለ የተለያዩ የገበያ ስፍራዎች እንደታዘብነው እና ሸማቾች እና ነጋዴዎች እንደገለፁልን፥ በተለይም ከውጭ በሚገቡ የምግብ ነክ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ታይቷልምስል Million Haileslasse/DW

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው፤ ተስፋና ስጋቱ


ሸማቾችም እንዲሁ በውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ከተደረገ በኃላ በተለያዩ ምርቶች እና አገልግሎችን የዋጋ ጭማሪ እየታየ መሆኑ ያነሳሉ።

ሸማቹ አቶ ወልደ ገብርኤል ነጋሽ "እዚህ አግባብ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ አሁን የተፈጠረ አይደለም። በጦርነቱ ወቅት ጀምሮ የተለመደ ነገር አለ። የሆነ ወሬ በተሰማ ቁጥር ሸቀጥ ሰማይ ነው የሚደርሰው። የመንግስት ቁጥጥር ማነስም አለ። አሁን ዶላር ጨመረ ተብሎ ገበያው ተረብሿል። እንደ ተቀጣሪ ሰራተኛ ገቢያችን ላይ ጭማሪ ሳይኖር ሁሉ ነገር ጨምሯል። እኔ የምለው ሸማቹም የተጠየቀው መክፈል ሳይሆን ለምን ብሎ መጠየቅ አለበት፣ መንግስትም ይስራበት" ሲሉ ተናግረዋል።

የምርቶች ዋጋ ጭማሪ በአዲስ አበባ

በመቐለ በተለይም የንግድ እንቅስቃሴው በስፋት በሚታይበት ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ የአስተዳደር አካላት ነጋዴዎች ሰበብ ፈጥረው ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌለው የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ ክትትል እያደረጉ መሆኑ እና እርምጃዎችም እየተወሰዱ መሆኑ ይገልፃሉ። የቀዳማይ ወያነ ክፍለከተማ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ገብረፃድቃን ወልደትንሳኤ"እስካሁን ዶላር ጨመረ ብለው የዋጋ ንረት የፈጠሩ 23 ሱቆች አሽገናል። በተለይም የተለያዩ ሸቀጦች ማለትም ዘይት፣ ማኮሮኒ፣ ፓስታ፣ የፍርኖ ዱቄት እና ሌሎች ትኩረት አድርገን ቁጥጥር እያደረግን ነው። የታሸጉትም እነዚህ ናቸው። እርምጃ መውሰዳች በራሱ ገበያው አረጋግቶታል፣ ጭማሪው አቁሟል" ብለዋል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ 

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW