1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትኢትዮጵያ

ትግራይ ክልል 60 ከመቶ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ ተገለጠ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ረቡዕ፣ መስከረም 22 2017

ትግራይ ክልል በአዲሱ የትምህርት ዘመን ወደ ትምህርት ገበታ ይገባሉ ተብለው ከተጠበቁ ተማሪዎች መካከል 60 በመቶ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ ተገለፀ። እንደ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ መረጃ 106 ትምህርት ቤቶች የተፈናቃዮች መጠልያ ሆነው እንዳሉ የገለፀ ሲሆን፤ ይህን ጨምሮ ሌሎች ችግሮች የትምህርት ሂደቱን እየጎዳ ነው ብለዋል ።

Äthiopien Tigray Bildung
ምስል Million Haile Selassie/DW

106 ትምህርት ቤቶች አሁንም የተፈናቃዮች መጠልያ ናቸው ተብሏል

This browser does not support the audio element.

በትግራይ ክልል በአዲሱ የትምህርት ዘመን ወደ ትምህርት ገበታ ይገባሉ ተብለው ከተጠበቁ ተማሪዎች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ ተገለፀ። እንደ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ መረጃ 106 ትምህርት ቤቶች የተፈናቃዮች መጠልያ ሆነው እንዳሉ የገለፀ ሲሆን፤ ይህን ጨምሮ ሌሎች ችግሮች የትምህርት ሂደቱን እየጎዳ ነው ብለዋል ።

በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ከፍተኛ ውድመት ከደረሰባቸው መካከል የትምህርቱ ዘርፍ እና አጠቃላይ የትምህርት መሰረት ልማቱ አንዱ ነው። በትግራይ ክልል ትምህርት ለዓመታት ተቋርጦ ከጦርነቱ መቆም በኋላ በይፋ የተጀመረ ሲሆን፤ የሚጠበቀው መጠን ተማሪ ግን አሁንም ወደ ትምህርት ገበታው እንዳልተመለሰ ይገለፃል።

እንደ የትግራይ ትምህርት ቢሮ መረጃ በዘንድሮው 2017 ዓመተምህረት የትምህርት ዘመን በአጠቃለይ 2 ነጥብ 5 ሚልዮን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ሊገቡ ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ይሁንና እስካሁን ከአንድ ሚልዮን በታች አልያም 40 በመቶ ተማሪ ብቻ መመዝገቡ ዐሳውቋል። መፈናቀል፣ ለትምህርት ያለ ፍላጎት መውረድ፣ የትምህርት መሰረተ ልማትና ግብአት አቅርቦት እጦት ከሚጠበቁት 60 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታው እንዳይመለሱ እንዳደረጋቸው ተነግሯል።

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ረዳኢ ገብረእግዚአብሔር እንዳሉት በሁሉም የትምህርት ደረጃ እና የተማሪዎች ዕድሜ፥ በከፍተኛ መጠን የሚስተዋል ወደ ትምህርት አለመመለስ እንዳለ የሚገልፁ ሲሆን ይሁንና ይህ በህፃናት ተማሪዎች ወደ ትምህርት መመለስ መጠን ግን የከፋ መሆኑ ይናገራሉ።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ  ምክትል ኃላፊ አቶ ረዳኢ ገብረእግዚአብሔር በተማሪዎች ምዝገባ እንደታዘብነው አጠቃላይ የተዘገቡ ተማሪዎች 40 በመቶ ደረሰ ብንልም፣ ከፋፍለን ስናየው እስካሁን የተመዘገቡ ህፃናት ተማሪዎች መጠን ከ20 በመቶ አይዘልም። ከሚጠበቁ ህፃናት ተማሪዎች መካከል 80 በመቶ ወደ ትምህርት ገበታ አልመጡም። ለትምህርት ያለው ፍላጎት በነበርንበት ጦርነት ምክንያት ተሸርሽሮ ያለበተ ሁኔታ ነው ያለው። ስነልቦናው ለመመለስ ሥራ ይፈልጋል። ይህ ለማድረግ መንግስት፣ በጎ አድራጊዎች መወጣት ያለባቸው ኃላፊነት እንዳለ ሆኖ አካባቢያዊ መፍትሔ ማበጀት ይገባል የሚል መነሻ ነው ያለው" ብለዋል።

ትግራይ ክልል 60 ከመቶ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም ተብሏልምስል Million Haile Selassie/DW

እንደ የትግራይ ትምህርት ቢሮ መረጃ፥ በትግራይ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል 106 የሚሆኑት አሁንም የተፈናቃዮች መጠልያ መሆናቸው፣ ሌሎች ከ500 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ከትምህርት ቢሮው ቁጥጥር ውጭ መሆናቸው ይገልጿል። የትምህርት ቢሮው ምክትል ሐላፊ በሰጠው መግለጫ በአንዳንድ አካባቢዎች እየታየ ነው ያሉት የትምህርት ማደናቀፍ ተግባራት ያነሱ ሲሆን በተለይም በአላማጣ እና ሌሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ከተማሪዎች ምዝገባ፣  በቋንቋ ማስተማር ጋር የተያያዙ ችግሮች መፍትሔ ይሻሉ  ብለዋል።

ትናንት በአላማጣ ከተማ በትምህርት ቤት አካባቢ የተከሰተው ሁከት ለሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑ መዘገቡ ይታወሳል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW