1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትግራይ ክልል 7 ወራት ያለ ነዳጅ

ዓርብ፣ የካቲት 4 2014

ላለፉት ሰባት ወራት ወደ ትግራይ ክልል የገባ የነዳጅ አቅርቦት ባለመኖሩ የመጓጓዣ አገልግሎት አስቸጋሪ ነው ተባለ። መቐለን ጨምሮ በአብዛኞቹ የትግራይ ክልል ከተሞች በሞተር የሚሠራ የተሽከርካሪ መጓጓዣ አገልግሎት የለም፤ አልያም ተወዷል።

Äthiopien | Tigray | Treibstoff Versorgungsengpässe
ምስል Million Haileselassie/DW

በትግራይ ክልል ከተሞች እንቅስቃሴ ተቀዛቅዟል

This browser does not support the audio element.

ላለፉት ሰባት ወራት ወደ ትግራይ ክልል የገባ የነዳጅ አቅርቦት ባለመኖሩ የመጓጓዣ አገልግሎት አስቸጋሪ ነው ተባለ። መቐለን ጨምሮ በአብዛኞቹ የትግራይ ክልል ከተሞች በሞተር የሚሠራ የተሽከርካሪ መጓጓዣ አገልግሎት የለም፤ አልያም ተወዷል። በእንስሳት ጉልበት የሚንቀሳቀሱ ጋሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ነዳጅ የማይሹ የመጓጓዣ አማራጮች በትግራይ ክልል ከተሞች በስፋት ዕንደሚታዩ የመቐለው ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ዘግቧል። ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘም የተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ ይገኛል ብሏል። በኮንትሮባንድ አለያም በሌላ ኢ-መደበኛ መንገድ የሚገባ አለያም ተከማችቶ የቆየ የተባለ ነዳጅ በመቀለ በጥቁር ገበያ በውድ ዋጋ እንደሚሸጥ፤ አንድ ሊትር ቤንዚን እስከ ስድስት መቶ ብር እንደገባም ተገልጧል። 

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW