1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትግራይ፤ ዛሬም ድንኳን ዉስጥ የሚኖሩት የጦርነት ተፈናቃዮች

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 29 2017

በትግራይ የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የጦርነቱ ተፈናቃዮች አሁንም በመጠልያዎች ዉስጥ ናቸው። ተፈናቃዮቹ መንግስት ረስቶናል፣ በበሽታና ሌሎች ችግር እያለቅን ነው የሚሉ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት በአስቸኳይ ወደቀዬአቸው ሊመልሷቸው ጥሪ ያቀርባሉ። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ተፈናቃዮች ለመመለስ እቅድ አውጥቶ እየሰራ መሆኑ ይገልፃል።

ፎቶ ማህደር፤ የትግራይ ተፈናቃዮች ኑሮ
ፎቶ ማህደር፤ ዛሬም በድንኳን የሚኖሩ የትግራይ ተፈናቃዮች ምስል Million Haileselassie/DW

ትግራይ፤ ዛሬም ድንኳን ዉስጥ የሚኖሩት የጦርነት ተፈናቃዮች

This browser does not support the audio element.

ትግራይ፤ ዛሬም ድንኳን ዉስጥ የሚኖሩት የጦርነት ተፈናቃዮች

በትግራይ ጦርነቱ ከቆመ ከሁለት ዓመት በላይ ቢሆንም፥ በትግራይ የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የጦርነቱ ተፈናቃዮች አሁንም በመጠልያዎች ናቸው። ተፈናቃዮቹ መንግስት ረስቶናል፣ በበሽታና ሌሎች ችግር እያለቅን ነው የሚሉ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት በአስቸኳይ ወደቀዬአቸው ሊመልሷቸው ጥሪ ያቀርባሉ። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ተፈናቃዮች ለመመለስ እቅድ አውጥቶ እየሰራ መሆኑ ይገልፃል።

የትግራዩ ጦርነት ከቆመ ከሁለት ዓመት በላይ ቢቆጠርም፥ በጦርነቱ ምክንያት ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ግን በሀገር ውስጥ እና በሱዳን የተለያዩ መጠልያዎች መፍትሔ ሳያገኙ የከፋ ሕይወት መምራት ቀጥለዋል። በተለይም ከምዕራብ ትግራይ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር ከሚዋሰኑ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች በትግራይ የተለያዩ ከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ግዚያዊ መጠልያዎች አስቸጋሪ ኑሮ እየገፉ ሲሆን፥ ከዛሬ ነገ ትመለሳላችሁ በሚል የሚገባላቸው ተስፋም ሳይፈፀም ቀርቶ አስከፊ ኑሮ እየገፉ መሆኑ ይናገራሉ። ከዓብይ ዓዲ መጠልያ ያነጋገርናቸው ተፈናቃይ አቶ ብርሃነ ታፈረ፥ የተፈናቃይ ጉዳይ ጭራሽኑ እየተዘነጋ ነው በማለት ቅሬታቸው ይገልፃሉ።

ሌላው ከፀገዴ ተፈናቅለው በሽረ ፀሃዬ ትምህርት ቤት ያነጋገርናቸው ተፈናቃይ አቶ ነጋሲ ማረከ በበኩላቸው፥ ወደቀዬው ያልተመለሰው ተፈናቃይ በረሃብ እና በሽታእያለቀ ነው በማለት መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሱላቸው ጥሪ ያቀርባሉ።

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ተፈናቃዮች ለመመለስ ጥረት ላይ መሆኑ የሚገልፅ ሲሆን፥ ለዚህ ማስፈፀሚያ ዝርዝር እቅድ መውጣቱ፥ ሂደቱ ለማስፈፀም ደግሞ 2 ነጥብ 1 ቢልዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ በቅርቡ ይፋ አድርጓል። ግዚያዊ አስተዳደሩ በዚህ እቅድ ዙርያ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት እና ከሌሎች ባለድርሻ የተባሉ አካላት ጋር እየተነጋገረ መሆኑ ተመላክቷል። የትግራይ ማሕበራዊ እና መልሶ ማቋቋም ጉዳዮች ቢሮ ሐላፊ ጀነራል ዘውዱ ኪሮስ፥ በትግራይ በኩል የተያዘው እቅድ ለማስፈፀም ከፌደራሉ መንግስት ጋር መግባባቶች እንደሚጠበቁ በዚህ ጉዳይ ዙርያ በተዘጋጀ መድረክ ተናግረዋል።

በትግራይ ስላሉ ተፈናቃዮች ጉዳይ ተደጋጋሚ መድረኮች ቢካሄዱም፣ መግባባት ተደርሷል ተብሎ በተደጋጋሚ ቢገለፅም፣ በተደጋጋሚ ቀነ ቀጠሮ ተቆርጦ ቢነገርም እስካሁን የታየ ለውጥ የለም።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW