ትግራይ ድንበር ተሻጋሪ የአምበጣ መንጋ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 19 2012
ማስታወቂያ
ድንበር ተሻጋሪ የበርሃ አምበጣ መንጋ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሮ ሀብትና ሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ የበርሃ አምበጣ መንጋው በተለይም በትግራይ ክልል አምስት ወረዳዎች መታየቱ የተገለፀ ሲሆን፤ ሕዝብ በባህላዊ መንገድ ለመከላከል እና አንበጣዎቹን ለማባረር እየተረባረበ ነው።፡ መንግስት በበኩሉ በተመረጡ አካባቢዎች በአውሮፕላን የታገዘ ፀረ ተባይ ኬሚካል ርጭት እያደረገ መሆኑ ገልፅዋል፡፡ የመቀሌው ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለሥላሴ ትናንት ወደ አዲ ጉደም ተጉዞ ኅብረተሰቡ የአንበጣ መንጋውን ለማረባረብ ሲጣጣር ተመልክቶ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ