1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቻይና፤ በቃጠሎ 38 ሰዎች ሞቱ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 13 2015

በማዕከላዊ ቻይና በሚገኝ አንድ ፋብሪካ ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ 38 ሰዎች መሞታቸዉ ተነገረ። በቻይናዋ ሄናን ግዛት በምትገኘዉ በአናንግ ከተማ በተነሳዉ ቃጠሎ ሌሎች ሁለት ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የቻይና መንግስት መገናኛ ብዙኃኖች ዘግበዋል።

China Anyang | Feuer in Fabrik
ምስል CCTV/AP/picture alliance

 

በማዕከላዊ ቻይና በሚገኝ አንድ ፋብሪካ ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ 38 ሰዎች  መሞታቸዉ ተነገረ።  በቻይናዋ ሄናን ግዛት በምትገኘዉ በአናንግ ከተማ በተነሳዉ  ቃጠሎ ሌሎች ሁለት ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የቻይና መንግስት መገናኛ ብዙኃኖች ዘግበዋል። የእሳት አደጋዉ የመገጣጠምያ መሣሪያዎችን "ሕገ ወጥ" በሆነ መንገድ በመጠቀም መቀስቀሱን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃኖች ዘግበዋል። ከስፍራዉ በወጡ ነገርግን ያልተረጋገጡ በተባሉ ዘገባዎች መሰረት ፤ አካባቢዉ ላይ የኬሚካል ቁሳቁሶች ተከማችተዉ  ነበር። በቻይና አብዛኛውን ጊዜ በቸልተኝነት አልያም የደህንነት መመሪያዎችን ባለመከተል ምክንያት በኢንዱስትሪ አካባቢዎች ይህን መሰል የእሳት አደጋና  እንደሚከሰተም ተመልክቷል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW