1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቻይና በጅቡቲ የጦር ሰፈር ለማቋቋም ዉል ተፈራረመች

ሐሙስ፣ ኅዳር 23 2008

ቻይና ጅቡቲ ላይ የጦር ሠፈር ለማቋቋም የአስር ዓመት ዉል ተፈራረመች። ቻይና ይህን ጦር ሠፈር ለማቋቋም ያሰበችዉ አካባቢዉ ላይ የሚገኘዉን የባሕር ላይ ዉንብድና ለመግታት መሆኑ ነዉ የተመለከተዉ።

Dschibuti Hafen
ምስል DW/J. Jeffrey


ከቀይ ባህርና ስዊዝ ካናል አቅራቢያ የምትገኘው ጅቡቲ ከቻይና የመጣውን ወዳጅነት አጥብቃ የምትሻው ትመስላለች። በሌላ በኩል በአፍሪቃ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ላይ የምትገኘዉ ቻይና እንዲህ ያለዉን ርምጃ የወሰደችዉ በአፍሪቃ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎችዋን ጥቅምና ከአገራቱ ጋር ያላትን ጥቅም ለማስጠበቅ መሆኑን ነዉ የተመለከተዉ። ቻይና ከአፍሪቃ ሃገራት ጋር ያላትን ትስስር ለማጠናከርም የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ ማክሰኞ ዕለት በዚምባቡዌ የጀመሩትን ጉብኝት ከነገ ጀምሮ ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ላይ ለሁለት ቀናት የሚካሄደዉን የአፍሪቃ ቻይና ጉባኤ በተባባሪ ሊቀመንበርነት በመምራት ያጠናቅቃሉ። በትንሺቱ የአፍሪቃ ቀንድ አገር በጅቡቲ እስካሁን ፈረንሳይ፤ ጃፓን እና ዩ.ኤስ አሜሪካ የጦር ሰፈር ያላቸው ሃገራት ናቸዉ። አሁን ደግሞ የአስር ዓመት ዉልን የተፈራረመችዉ ቻይና በጅቡቲ የጦር ሠፈር የሚኖራት አራተኛዋ አገር ትሆናለች። እዚህ ስቱድዮ ከመግባቴ ጥቂት ሰዓታት በፊት ቻይና ከጅቡቲ ጋር ስለተፈራረመችዉ ዉልና አንድምታዉ ናይሮቢ ከሚገኘዉ ጋዜጠኛ ጋር ተወያይቼ ነበር።

ፋሲል ግርማ


አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW