ቻይና፤ የግብፅና የቱኒዚያ ንቅናቄ አስግቷታል
ረቡዕ፣ የካቲት 9 2003ማስታወቂያ
በእርግጥ ለቻይናውያኑ በግብፅና በቱኒዚያ የተቀጣጠሉት ህዝባዊ አመፆች አዲስ አይደሉም። ቻይናውያን ከፍተኛ መስዋዕት ያስከፈላቸውን ታላቅ ንቅናቄ የዛሬ 22 ዓመታት ግድም እዛው ቻይና ውስጥ ፈፅመውታልና። ያኔ ኮሚኒስት መራሹ የቻይና መንግስት ሰላማዊ ሰልፈኞቹን በጅምላ ነው የጨረሰው። እንደ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ገለፃ ከሆነ፤ በወቅቱ ቻይና ውስጥ 3000 ሰዎች በንቅናቄው ሂደት ተገድለዋል። ያን እልቂት ብዙዎች ዛሬም ድረስ የ«ቲየን አን ሜን ፍጅት» በማለት ያስውሱታል። ከቲየን አን ሜኑ ፍጅት በኋላ ግን ቻይናውያን በፍርሀት ተሸብበው አልተቀመጡም። ዛሬ ልክ እንደ ግብፃውያኑና ቱኒዚያውያኑ ሁሉ ኢንተርኔትን በመጠቀም በከፍተኛ ሁኔታ እየተወያዩ ነው።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ