1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ችግረኛ ቤተሰቦችን ለመደገፍ የተነሳው ወገኔ የኢትዮጵያውያን መረዳጃ

ረቡዕ፣ ኅዳር 22 2014

መቀመጫውን ዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ ያደረገው ወገኔ የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ማሕበር ኑሮ የከበዳቸው ቤተሰቦችን ከችግር ለማላቀቅ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ። ማሕበሩ በሚገኘው ገቢ ለችግር የተጋለጡ ቤተሰቦች በተለያዩ ሙያዎች ሰልጥነው ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ ለማስቻል አቅዷል።

Logo Wegene Foundation

ወገኔ የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ማሕበር

This browser does not support the audio element.

መቀመጫውን ዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ ያደረገው ወገኔ የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ማሕበር ኑሮ የከበዳቸው ቤተሰቦችን ከችግር ለማላቀቅ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ። የማሕበሩ መሥራችና ኘሬዝደንት ወይዘሮ ኒኒ ለገሠ በተለይ ለዶይቸ ቨለ እንደገለፁት ማሕበሩ የቆመለትን ግብ ለማሳካት በአሜሪካን ሀገር የመስጠት ማክሰኞ ዕለትን በመንተራስ ትናንት ገቢ የማሰባሰብ መርሐግብር አካሄዷል። ማሕበሩ በሚገኘው ገቢ ለችግር የተጋለጡ ቤተሰቦች በተለያዩ ሙያዎች ሰልጥነው ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ ለማስቻል አቅዷል። የአትላንታው ዘጋቢያችን ታሪኩ ኃይሉ የማሕበሩ መሥራችና ፕሬዝደንት በማነጋገር ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።

ታሪኩ ኃይሉ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW