ችግር ወደ አስጠኚነት የመራው ሔኖክ
ዓርብ፣ ነሐሴ 20 2008ማስታወቂያ
ዶ/ር ሔኖክ ወንድይራድ በፕሬዝዳንት ኦባማ የተመሰረተው ወጣት አፍሪቃውያን መሪዎች የስልጠና እድል ተጠቃሚ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ ነው። ወጣቱ ማክ አዲስ አስጠኚ በተሰኘ ተቋሙ በኩል ተማሪዎችን ከአስጠኚዎች ጋር ያገናኛል። ድርጅቱ ከመዋዕለ-ህጻናት እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚገኙ ተማሪዎች ብቃት እና ሥነ-ምግባር ያላቸውን አስጠኚዎች ያገናኛል። የቋንቋ እና የሙዚቃ መሳሪያዎች አስጠኚዎችም በሔኖክ በኩል ሊገኙ ይችላሉ። ሔኖክ በኢትዮጵያ የተካሄዱ የጀማሪ ኩባንያዎች ውድድር አሸንፎ የገንዘብ ሽልማት አግኝቷል።
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ