1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ግጭት ውስጥ የሰነበተው ሞያሌ እና አካባቢው መረጋጋት እያሳየ ነው ተባለ

ሥዩም ጌቱ
ቅዳሜ፣ ኅዳር 19 2019

በሞያሌ ከተማ እና አካባቢው የሰነበተው የጸጥታ መደፍረስ እያተረጋጋ ነው ተባለ

ግጭት ውስጥ የሰነበተው ሞያሌ እና አካባቢው መረጋጋት እያሳየ ነው ተባለ
ግጭት ውስጥ የሰነበተው ሞያሌ እና አካባቢው መረጋጋት እያሳየ ነው ተባለምስል፦ Michael Kwena

በሞያሌ ከተማ አንጻራዊ መረጋጋት መፈጠሩን ነዋሪዎች ተናገሩ

This browser does not support the audio element.

ከአንድ ወር በላይ  ለዘለቀ ጊዜ አለመረጋጋት ውስጥ የሰነበተችው የሞያሌ ከተማ ከትናንት በስቲያ ሓሙስ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ የፌዴራል የጸጥታ ኃይሎች መሰማራታቸውን ተከትሎ ተኩስ መቆሙ ተነግሯል፡፡

አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች በሞያሌ የተኩስ ድምጽ መቆሙን ተከትሎ እስከ ዛሬ ቅዳሜ ድረስ አንጻራዊ መረጋጋት መታየቱን ተናግረዋል፡፡

ከትናንት በስቲያ ሓሙስ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በስፋት ከተማዋ ውስጥ በመሰማራታቸው ተፋላሚዎች ተኩስ እንዲያቆሙ ማዘዛቸው ተሰምቷል። የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን አቋርጦ ወደ ኬንያ በሚያልፈው አውራ ጎዳና ላይ በስፋት ሲንቀሳቀሱ ማየታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።  

በኦሮሚያእናሶማሊክልሎች አዋሳኝ እንዲሁም ኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር ላይ የምትገኘው የንግድ ከተማዋ ሞያሌ ወደ ዘላቂ ሰላም ለመመለሷ ለጊዜው ማረጋገጫ ባይገኝም፤ የመሳሪያ ድምጽ በዚህ ሶስት ቀናት ተከታትሎ መቆሙን ተከትሎ ግን ከተማዋ ውስጥ ሻል ያለ እንቅስቃሴ መታየቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ እና ኬንያ የድንበር ከተማዋ ሞያሌ ለሳምንታት ቀትሎ የቆየው ግጭትና የከባድ መሳሪያዎች ልውውጥ በጊዜያዊ የተኩስ አቁሙ ለጊዜውም መገታቱ የተሰማው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኃይል አከባቢውን ለማረጋጋት ከትናንት በስቲያ ሓሙስ ስፍራው ላይ መድረሱን ተከትሎ ነው፡፡

ከባለፈው ሓሙስ ጀምሮ በከተማዋ ተኩስ አቁም የታወጀበትን መንገድ ለዶይቼ ቬለ የገለጹት የአይን እማኝ የከተማዋ ነዋሪ፤ “የፌዴራል ፖሊስ ገብተው በሁለቱም በኩል አቁሙ ሀገር ሰላም ነው አሉ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን አቋርጦ ወደ ኬንያ በሚያልፈው አውራ ጎዳና ላይ በስፋት ሲንቀሳቀሱ ማየታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።  ምስል፦ Patrick Ngugi/AP Photo/picture alliance

 

የተኩስ አቁሙ ከታወጀና የመሳሪያ ድምጸጽ ከሰማን ይሄው አሁን ሶስተኛ ቀናችን ነው፡፡ በርግጥ አሁን የአፈሙዝ አፍ ከተዘጋ ወዲህ የተወሰነ አንጻራዊ የሆኑ መረጋጋቶች በከተማዋ ውስጥ ታይተዋል፡፡

ወደ ኬንያ የሚወስደው ትልቁ የፌዴራል መንገድን ጨምሮእንቅስቃሴው ግን ገና ወደ ቦታው አልተመለሰም፡፡ ጉምሩክ ደርሰው መንገድ ቀይረው የሚወጡ ተሽከርካሪዎች ግን አሉ፡፡

የባጃጅ እንቅስቃሴም ከተማ ውስጥ ካለፉት ሳምንታት ሻል ብሏል፡፡ ተኩስ ቢቆምም ገና ሶስተኛ ቀኑ በመሆኑ የተለመደው እንቅስቃሴ ግን የለም” ብለዋል፡፡

በዋናው የፌዴራል መንገዱ ላይ በስፋት የሚታዩት የፌዴራል ፖሊስ ፓትሮል ናቸው የሚሉት ሌላው አስተያየታቸውን ያጋሩን የከተማዋ ነዋሪ በፊናቸው ዛሬ በተሻለ መልኩ እንቅስቃሴ ብታይም መረጋጋት መጥቷል የሚያስብል ነገር ግን እስካሁን አለመመልከታቸውን ነው የገለጹት፡፡

“ፌዴራል በመሃል ከገባ በኋላ ከተማዋ አሁን ጸጥ ብላለች፡፡ ሁሉም አርፈው ተቀምጠዋል፡፡ ተኩስም ቆሟል፡፡ በዋናው አስፋልት ላይ የፌዴራል ፖሊስ ፓትሮሎች ናቸው በስፋት የሚታዩት እንጂ የተለመደው እንቅስቃሴ ገና አልተጀመረም፡፡ ለውጥ የለም ለጊዜው” ብለዋል፡፡

የተኩስ አቁሙ ከታወጀና የመሳሪያ ድምጸጽ ከሰማን ይሄው አሁን ሶስተኛ ቀናችን ነውምስል፦ Michael Kwena

 

ነዋሪዎቹ አክለውም፤ “አሁን የከፋ ነገር አይታይም፡፡ ነገር ግን የተፈናቀለ ሰው ወደ ቤቱ እንዲመለስ ድረስ የሚያደርስ ጥሪም ሆነ እንቅስቃሴ ገና አልተጀመረም፡፡ አሁን ጦርነቱ ይቁም የሚል ነገር ብቻ ነው የሚታየው፡፡ በከተማው አሁን ያልወጣና ያልተሰደደ ሰው ንብረቱ ላይ የደረሰውን ጉዳት ዞሮ እየተመለከተ ነው፡፡ የንግድም ሆነ ሌላው አገልግሎት ግን ገና አልተጀመረም” ብለዋል፡፡

ያዝ ለቀቅ እያለ የቀጠለው የድንበር ከተማዋ ሞያለ የጸጥታ ችግር በርካቶችን ከቀዬው በማፈናቀል ብርቱ ማህበራዊ ቀውስን አስከትሏል፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ ያጋሩት በአከባቢው ላይ ጥናት ያደረጉ አጥኚ ጉዮ ዶዮ እንደሚሉትም አልፎ አልፎ ችግር የሚፈጥረው የአከባቢው ግጭት ዘላቂ እልባት እንዲያገኝ ከኢትዮጵያም የተሻገረ የአከባቢው አገራት የተቀናጀ ስራ ያስፈልጋል ይላሉ፡፡

“ተንከባሎ የመጣ መፍትሄ የሚፈልግ ችግር ቢኖርም የሞያሌ የጸጥታ ችግሩ መንስኤ ውስብስብ አይደለም” የሚለውን አስተያየት የሰጡት አትኚው፤ በኮንትሮባንድ ንግድ ተወሳስቦ እስከ ሰሜን ኬንያ ድረስ የሚሳብ ነው ያሉት ችግር ከመሰረቱ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያን በማሳተፍ ችግሩ ከመሰረቱ መፈታት ይኖርበታል የሚል ምክረሃሳብ ሰጥተዋል፡፡

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

 

Edited by:Tamirat Dinssa Geleta ታምራት ዲንሳ ገለታ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW