1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ኒኮላ ሳርኮዚ ፤ በፈረንሳይ ታሪክ ዘብጥያ የወረዱ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት

ረቡዕ፣ ጥቅምት 12 2018

በተፈረደባቸው የ5 ዓመት የእስር ቆይታ በሙሉ ሳርኮዚ ከታሰሩበት ክፍል አጠገብ ሆነው በቋሚነት ሁለት ፖሊሶች እንደሚጠብቋቸው የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ላውረን ኑኔስ ዛሬ ተናግረዋል። የሳርኮዚ የእስር ጊዜ እንዲያጥር ይግባኝ ያሉት ጠበቆቻቸው በአንድ ወር ውስጥ ሊፈቱ ይችላሉ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ።

በፓሪሱ ላ ሶንት ወህኒ ቤት የታሰሩት የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዚ
በፓሪሱ ላ ሶንት ወህኒ ቤት የታሰሩት የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዚምስል፦ Julien De Rosa/AFP/Getty Images

ኒኮላ ሳርኮዚ ፤ በፈረንሳይ ታሪክ ዘብጥያ የወረዱ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት

This browser does not support the audio element.

ፈረንሳይን ከጎርጎሮሳዊው 2007 እስከ 2012 ዓ.ም. የመሩት የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንትኒኮላ ሳርኮዚስልጣን ከመያዛቸው በፊት ለምርጫ ዘመቻ ከሊቢያ ገንዘብ ለማሰባሰብ በመመሳጠር ተወንጅለው ትናንት እስር ቤት ገብተዋል። በተፈረደባቸው የ5 ዓመት የእስር ቆይታ በሙሉ ከታሰሩበት ክፍል አጠገብ በቋሚነት ሁለት ፖሊሶች እንደሚጠብቋቸው የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ላውረን ኑኔስ ዛሬ ለአንድ የፈረንሳይ ራድዮ ተናግረዋል። ሳራኮዚ ፕሬዝዳንት የነበሩ በመሆናቸው ጥበቃ የማግኘት መብት እንዳላቸው የተናገሩት ሚኒስትሩ ዛቻም ስለሚሰነዘርባቸው በተያዙበት ጥበቃ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።ክሱ ፖለቲካዊ ተነሳሽነት ያለው ነው ሲሉ የሚሟገቱት ሳርኮዚ ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ሲያስተባብሉ ቆይተዋል።  የሳርኮዚ የእስር ጊዜ እንዲያጥር ይግባኝ ያሉት ጠበቆቻቸው በአንድ ወር ውስጥ ሊፈቱ ይችላሉ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ።

 

የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዚ የታሰሩበት ፓሪስ የሚገኘው የላ ሶንት እስር ቤት ምስል፦ Tom Nicholson/REUTERS

ስለ ሳርኮዚ እስር ፣ይግባኝ እና ወደፊት ስለሚጠበቀው፣የፓሪስዋን ዘጋቢያችንን ሃይማኖት ጥሩነህን በስልክ አነጋግረናል። 
ሃይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW