1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ናሚቢያ ውስጥ በልጅነት መዳር ያስከፈለው ዋጋ

03:15

This browser does not support the video element.

ማክሰኞ፣ ግንቦት 29 2015

ብዙ ጥያቄዎችን ከሚያነሱ ባህላዊ ልምዶች አንዱ በልጅ እድሜ የሚደረግ ጋብቻ ነው። ሂልዳ ማፉታ በ16 ዓመቷ ከአንድ ትልቅ ሰው ጋር በትዳር አብራ ለመኖር ተገዳ ነበር። ዛሬ የ21 ዓመቷ ናሚቢያዊት ህይወቷን እንዴት እንደቀየረች ታሪኳን ለዶይቸ ቬለ አጋርታለች።

እ.ጎ.አ. ጥቅምት 29 ቀን 2020 በጾታ እኩልነት ፣ ድህነትን ማጥፋት እና ማህበራዊ ደህንነት ላይ የሚሰራው የናሚቢያ ሚኒስቴር (MGEPESW) ይፋ ያደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በሀገሪቱ ካሉ ልጃገረዶች 18.4% ያህሉ ያለ እድሜያቸው ይዳራሉ።  ወንዶች ደግሞ 4.1 % ያህል ናቸው። ጥናቱ እንደሚጠቁመውም በአገሪቱ ውስጥ ያሉ በርካታ ታዳጊ ሴቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ከ12 እስከ 17 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ይፈጽማሉ። በልጅነት ከተዳሩ ልጃገረዶች በእድሜ ትንሽ የሚባሉት በ11 ዓመታቸው የተዳሩ ናቸው። ድህነት፣ ባህልና የትምህርት እድል አለማግኘት ብዙውን ጊዜ የልጅ ጋብቻ እንዲፈፀም ዋና ምክንያቶች ናቸው።  #77ከመቶው
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW