ኔቶ ቱርክ እና የፓትሪየት ሚሳይል
ማክሰኞ፣ ኅዳር 25 2005ማስታወቂያ
የምትችል «ፓትሪየት» የተባለውን ፀረ ሚሳይሉን ሮኬት እንዲያቀርብላት ከሁለት ሣምንት በፊት ባቀረበችው ጥያቄ ላይ ዛሬ መከሩ። ከምክክሩ በኋላ ኪዳኑ ፓትሪየት ፀረ ሚሳይሉ ሮኬት በቱርክ እንዲተከል ወስኖዋል። እስካሁን የዚሁ እጅግ ዘመናይ የሆነው የ«ፓትሪየት» መሣሪያ ባለቤት የሆኑት ሦስት ሀገራት ጀርመን፡ ኔዘርላንድስ እና ዩኤስ አሜሪካ ብቻ ሲሆኑ፣ ጀርመን ይህንኑ የጦር መሣሪያ ለቱርክ ለመስጠት ዝግጁ መሆንዋን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቬለ ቀደም ሲል ገልጸዋል። ፀረ ሚሳይሉ ሮኬት ለቱርክ ከመስጠቱ ጥያቄ ጋ በተያያዘው የጀርመን ወታደሮች ሥምሪት ላይ የጀርመን ፌዴራዊ ምክር ቤት በዚህ ወር ውሳኔ ማሳለፍ ይኖርበታል። ቱርክ በጎረቤት ሶርያ የቀጠለው የርስበርስ ጦርነት ለሀገርዋ ፀጥታ ስጋት እንደደቀነ ተሰምቶታል። ስለ ሚሳኤል ተከላው አስፈላጊነት እንዲሁም የሶሪያውን የርስ በርስ ጦርነት ለማቆም በሚደረገው ጥረት ላይ ሊሳድር ስለሚችለው ተፅእኖና ስለሩስያ አቋም የብራሰልሱን ወኪላችንን ገበያው ንጉሴ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ገበያው ንጉሴ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ