1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አልሻል ያለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ መፍትሄው ምን ይሆን ?

ሐሙስ፣ ነሐሴ 9 2016

አበበ ቢቂላ ፤ ምሩጽ ይፍጠር ፤ ሃይሌ ገብረ ስላሴ ፤ ቀነኒሳ በቀለ፤ ደራርቱ ቱል እና ጥሩነሽ ዲባባ እና ሌሎችን ጨምሮ ስማቸውን በደማቁ ያስጻፉ አንጋፋ አትሌቶችን ያፈራች ፤ አትሌቲክስ የባህል ያህል የዳበረባት ሀገር ውድድሮች በሚካሄዱባቸው ዓለማቀፍ መድረኮች ከነበረችበት ስፍራዋ እየለቀቀች ፤ ዉጤት እንደከዳት ቀጥላለች ።

Olympia Paris 2024 - Schlussfeier
ምስል Athit Perawongmetha/REUTERS

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ዉጤት ቁልቁል መሄዱ አሳስቦናል ፤ ባለሞያዎች

This browser does not support the audio element.

 

ሃገራት በአህጉራዊም ሆነ በዓለማቀፍ ደረጃ ከብር እና ከፍታቸውን ከሚገልጡባቸው ማህበራዊ ጉዳዮች መካከል ስፖርት አንዱ ነው። እግር ኳስን ጨምሮ አትሌቲክስ እና ሌሎችም የስፖርት መስኮች አሁን አሁን ለሃገራት ከክብር እና ዝና መገለጫነት ባሻገር የኤኮኖሚ መሰረትም እየሆኑ መጥተዋል። ምስራቅ አፍሪቃዊቷ  ሀገር ኢትዮጵያ በዓለማቀፍ ደረጃ በተለያዩ አጋጣሚዎች ስሟ በረሃብ እና ጦርነት የመጠራቱን ያህል በተለይ በአትሌቲክስ ውድድሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥሩ ስም እና ዝና ካተረፉ ሃገራት ተርታ አስመድቧታል ፤ በተለያዩ ዓለማቀፍ ስፖርታዊ ዝግጅቶችም ሰንደቅ ዓላማዋ ከፍ ብሎ ተውለብልቧል።

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ውጤት

አበበ ቢቂላ ፤ ምሩጽ ይፍጠር ፤ ሃይሌ ገብረ ስላሴ ፤ ቀነኒሳ በቀለ፤ ደራርቱ ቱል እና ጥሩነሽ ዲባባ እና ሌሎችን ጨምሮ  ስማቸውን በደማቁ ያስጻፉ አንጋፋ አትሌቶችን ያፈራች ፤ አትሌቲክስ የባህል ያህል የዳበረባት ሀገር  ውድድሮች በሚካሄዱባቸው ዓለማቀፍ መድረኮች ከነበረችበት ስፍራዋ እየለቀቀች ፤ ዉጤት እየከዳት እና ትናንትን እየናፈቀች ቀጥላለች ።

አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በፓሪስ ኦሎምፒክ ኦሎምፒክ ለመሳተፍ በተጠባባቂነት ከተጓዙት አትሌቶች አንዷ ናት ።

በስልጠና ወቅት  ለአትሌቶች ተገቢ ክትትል እና ድጋፍ አለመደረጉ የሚጠበቀው ዉጤት እንዳይገኝ ምክንያት ሆኗል ትላለች።

የ33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ ፍጻሜ እና ኢትዮጵያ

 

«ማንኛውም የስፖርት ወዳጅ ማለት ነው ፤ ውድድር ሲደርስ ብቻ ነው እንጂ መጀመሪያ አትሌት የት እንዳለ ፤ ምን ላይ እየሰራ እንዳለ ትኩረት ሰጥቶ የሚመለከት የለም »

አሰልጣን ሃጂ አዲሎ የማራቶን አሰልጣኝ ናቸው ፤ በማራቶን የተሻለ ውጤት መመዝገቡን የሚገልጹት ሃጂ ኢትዮጵያ በምትታወቅባቸው የአምስት እና አስር ሺ ሜትር ውድድሮች ቴክኒካዊ በነበሩ ስህተቶች የተጠበቁ ውጤቶች ሳይመጡ መቅረታቸውን ይገልጻሉ ፤ አትሌቶችን እንደቀደመው ጊዜ በብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አለመያዝ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮበታል።

ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ስፖርታዊ ክንዋኔዎች

«እውነት ለመናገር እንደነ አሰልጣኝ ገብረመስቀል ኮስትሬ በነበሩበት ጊዜ አትሌቶቹን በብሔራዊ ቡድን ይዞ ማሰራት ቀላል ነው። አሁን የአትሌቶች ብዛትም ለዚህ ትንሽ እንቅፋት ሆኗል።»

ኑሮዋን እንግሊዝ ለንደን ያደረገችው ጋዜጠኛ አርአያት ራያ ኦሎምፒክን ጨምሮ በበርካታ ዓለማቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ በአካል በመገኘት የኢትዮጵያውያን የተሳተፉባቸውን ውድድሮች ተመልክታለች፤ ለተገኘው ዉጤትም  ሰፊ ሽፋን በመስጠት ትታወቃለች። በ33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ የተገኘው ዉጤት ከምንግዜዉም በላይ እንዳሳዘናት ትናገራለች።

በ33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ የተገኘው ዉጤት ከምንግዜዉም በላይ እዝናለሁምስል Privat

« እንደ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አዝኜ ነው ያለፍኩት ፤ የምትጠብቀው ነገር አለ፤ ከነበረህ ታሪክ አትሌቲክስ ላይ በተለይ ረዥም ርቀት ባህላዊ ስፖርታችን ነው ። በዚያው ስሜት ነው የምናየው ፤ በተፈጠረው ዉጤት አዝኛለሁ»

የሴቶች ማራቶን በፓሪስ ኦሎምፒክ

የኢትዮጵያ በኦሎምፒክ መድረክ የአትሌቲክስ ውድድር ተሳትፎ ወደ ጎርጎሪዮሱ 19 60ዎቹ ወደ ኋላ ይመልሰናል።  አበበ ቢቂላ በጣሊያን ሮም በባዶ እግሩ ሮጦ ለራሱ ፣ ለሀገሩ ብሎም ለአፍሪቃ እና ለመላው ጥቁሮች ኩራት የሆነውን  በማራቶን የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፎ ደማቅ ታሪክ ጽፏል። አበበ በሮም በኋላም በቶክዮ የደገመው አሸናፊነት እነ ማሞ ወልዴ እና ምሩጽ ይፍጠርን አስከትሎ እስከ የአሁኑ ባለድል የታምራት ቶላ ትውልድ ድረስ መዝለቅ ችሏል።

በበ በሮም በኋላም በቶክዮ የደገመው አሸናፊነት እነ ማሞ ወልዴ እና ምሩጽ ይፍጠርን አስከትሎ እስከ የአሁኑ ባለድል የታምራት ቶላ ትውልድ ድረስ መዝለቅ ችሏል።ምስል Spada/LaPresse/IMAGO

ይህ የአሸናፊነት እና የድል ቅብብል ግን እንዲሁ አልጋ በአልጋ በሆነ መንገድ እየተሸጋገረ የመጣ ሳይሆን በውጣ ዉረድ ውስጥ አንዳንዶች ለአስርት ዓመታት ጭምር ከአሸናፊነት እየተወጣ በትናንት ታሪክ እስከመጽናናት የተደረሰባቸው አጋጣሚዎች ጥቂት አይደ አይደሉም።

ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ለአዲስ ትውልድ መነሳት ምክንያት የነበረው እና ሳያቋርጥ የአትሌቶች መፍለቂያ ምድር እስከመባል ያደረሳት ታሪካዊ ድል የተመዘገበው በሲዲኒ ኦሎምፒክ ወቅት ነበር ። በወቅቱ ኢትዮጵያ 4 የወርቅ ሜዳሊያዎችን ስታሸንፍ አንድ የብር እና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችላለች ።

የዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ቅድመ ዝግጅት

 

ከሲዲኒ ኦሎምፒክ በኋላ በነበሩ የኦሎምፒክ ጫወታዎች በተለይ እንደነ ቀነኒሳ በቀለ ፤ ጥሩነሽ ዲባባ ፤ መሰረት ደፋር እና የመሰሳሰሉ ድንቅ አትሌቶች በ10 እና 5 ሺ ሜትር ውድድሮች ያስመዘገቧቸው ተከታታይ ውጤቶች  የኢትዮጵያዉያን ባህል ብቻ እስኪመስሉ አድርሷቸው ነበር ።

ከሲዲኒ ኦሎምፒክ በኋላ በነበሩ የኦሎምፒክ ጫወታዎች በተለይ እንደነ ቀነኒሳ በቀለ ፤ ጥሩነሽ ዲባባ ፤ መሰረት ደፋር እና የመሰሳሰሉ ድንቅ አትሌቶች በ10 እና 5 ሺ ሜትር ውድድሮች ያስመዘገቧቸው ተከታታይ ውጤቶች  የኢትዮጵያዉያን ባህል ብቻ እስኪመስሉ አድርሷቸው ነበር ።ምስል Reuters/H. Hanschke

አሁን ይህ ታሪክ እየሆነ የመጣ መስሏል። የኢትዮጵያዉያን መኩሪያ የሆነው አትሌቲክሱ በርግጥ ታሟል።

የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በምክትል ፕሬዚደንትነት የሚመራው  አትሌት ገዛኸኝ አበራ እንደሚለው በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራር ውስጥ የውጭ ዜጎች መካተታቸው በራሱ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ይናገራል።

የኢትዮጵያውያን አትሌቶች አንጸባራቂ ድል እና የአፍሪቃ ዋንጫ ፍጻሜ

ጋዜጠኛ አርአያት ራያ እንደምትለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ችግር ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ተያያዞ የመጣ ነው ። ለችግሩ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት ግን የአትሌቲክስ እና ኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ናቸው ባይ ናት ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለኦሎምፒክም ይሁን ለሌሎች አህጉራዊ እና አለማቀፍ ውድድሮች አትሌቶችን የሚመርጥበት መስፈርት ወጥነት ማጣት ለውጤት መታጣት አንዱ ምክንያት ተደደርጎ ሲነሳ በስፋት ይሰማል ። አትሌት ፍሬወይኒ እንደምትለው እርሷን ጨምሮ የተሻለ ዉጤት ሊያመጡ ይችሉ የነበሩ አትሌቶች ለውድድር ሳይበቁ የቀሩበት ምክንያቱ ይህ ነው ።

ጋዜጠኛ አርአያት ራያ እንደምትለው ከሆነ በሀገሪቱ የአትሌቲክስ ስፖርት ውድቀት መንግስት የራሱን ድርሻ መውሰድ እንዳለበት ነው።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለኦሎምፒክም ይሁን ለሌሎች አህጉራዊ እና አለማቀፍ ውድድሮች አትሌቶችን የሚመርጥበት መስፈርት ወጥነት ማጣት ለውጤት መታጣት አንዱ ምክንያት ተደደርጎ ሲነሳ በስፋት ይሰማል ። ምስል Haimanot Tiruneh/DW

በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ የኢትዮጵያ አትሌቶች በፈረንሳይ የሚለማመዱበት ቅድመ ሥምምነት ተፈረመ

አሰልጣኝ ሃጂ አዲሎ ችግሩ ጊዜ ሳይወድ ንግግር ሊደረግበታ ይገባል ባይ ናቸው ። መፍትሄውም በንግግር ውስጥ እንደሚገኝ በመጠቆም ።

መስከረም 2018 ጃፓን ቶኪዮ የምታስተናግደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አንድ ዓመት ቀርቶታል። በፓሪስ ኦሎምፒክ የጠፋው የኢትዮጵያዉያን ውጤት እንዲመለስ ካሁኑ ብርቱ ጥረት ይጠይቃል። አትሌቶች ከሚያደርጉት የግል እና የቡድን ዝግጅት ባሻገር ፤ ፌዴሬሽኑ ከህመሙ ለፈወስ እና ራሱን ለመፈተሽ በቂ ጊዜ ያለውም ይመስላል።

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW