1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አማራ ክልል አንፃራዊ ሠላም ሠፍኗል-ርዕሰ መስተዳድር

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 2 2015

ርዕሠ መስተዳድር አረጋ ከበደ የርዕሠ መስተዳድርነቱን ሥልጣን ከያዙ ወዲሕ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት የመንግስት ፀጥታ አስከባሪዎች የክልሉን የዞን ከተሞች በሙሉና አብዛኞቹን የወረዳ ከተሞችን ተቆጣጥረዋል

የማራ ክልል ምክር ቤት በጉባኤ ላይ-ባሕር ዳር መጋቢት 2015
የማራ ክልል ምክር ቤት በጉባኤ ላይ-ባሕር ዳር መጋቢት 2015ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች የርዕሰ መስተዳድሩን መግለጫ አልተቀበሉትም

This browser does not support the audio element.

 የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የፋኖ ታጣቂ ኃይላት ሲዋጉባቸዉ በነበሩት በአብዛኖቹ የአማራ ክልል አካባቢዎች አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ።ርዕሠ መስተዳድር አረጋ ከበደ  የርዕሠ መስተዳድርነቱን ሥልጣን ከያዙ ወዲሕ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት የመንግስት ፀጥታ አስከባሪዎች የክልሉን የዞን ከተሞች በሙሉና አብዛኞቹን የወረዳ ከተሞችን ተቆጣጥረዋል። የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች ግን የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ አገልግሎት መጪያ ተቋማና መንገዶች ተዘግተዉ ሠላም ሠፍኗል ማለት አይቻልም ይላሉ።የአማራ ክልል ውጊያ ወቅታዊ መረጃ

ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW