1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አማራ ክልል ከ4.7 ሚሊዮን ተማሪዎች አይማሩም

ሐሙስ፣ ኅዳር 19 2017

አማራ ክልል በፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚደረገዉ ዉጊያ4.7 ሚልየን ህፃንት መማር አለመቻላቸዉን የአማራ ክልል የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት መድረክ ወይም ፎረም አስታወቀ።መድረኩ እንደሚለዉ በክልሉ 969 የጤና ተቋማት ውድመት።

ጦርነቱ ወደ 1000 የሚጠጉ የጤና ተቋማት ማፈራረሱን ባለሙያዎችና ምሑራን አስታዉቀዋል
በአማራ ክልል በሚደረገዉ ጦርነት 4.5 ሚሊየን ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው የትምህርት ቤቶች ፈርሰዋል መምህራን ተሰደዋል  ምስል Alemnew Mekonnen/DW

  አማራ ክልል ከ4.7 ሚሊዮን ተማሪዎች አይማሩም

This browser does not support the audio element.

  

አማራ ክልል በፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚደረገዉ ዉጊያ4.7 ሚልየን ህፃንት መማር አለመቻላቸዉን የአማራ ክልል የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት መድረክ ወይም ፎረም አስታወቀ።መድረኩ እንደሚለዉ በክልሉ 969 የጤና ተቋማት ውድመት። በጦርነቱ የወደሙትን ተቋምማት መልሶ ለመገንባት አለማቀፍ ተቋማት  ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል።

4.7 ሚሊየን ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው የትምህርት ቤቶች ፈርሰዋል መምህራን ተሰደዋል  ቀየው በጦርነት እና በ ድሮን ጥቃት ታርሷል። 969 የሚደርሱ የክልሉ የጤና ተቋማት ወድመዋል  ይህ  ቁጥር በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የውደሙትን  አይጨምርም ።

የክልሉ የጤና ቢሮ እና ኢንስቲትዩት  ባደረጉት ጥናትና  ከአለም አቀፍ ተቋማት በሰበሰበው መረጃ  በክልሉ ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ካለፈው ዓመት ማብቂያ አንስቶ የመንግሥት ኃይሎች ቢያንስ 13 በሚደርሱ ከተሞች በጤና ተቋማት እና በሠራተኞች እንዲሁም በትራንስፖርት አገልግሎቶች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል ።

በአማራ ክልል ትምሕርት የሚሰጥባቸዉ ትምሕርት ቤቶች በከተሞች አካባቢዎች የሚገኙ ናቸዉ።ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕግ ሀገራት  በጦርነት ውስጥ ቢሆን እንኳን የህክምና ተቋማት፣ ባለሙያዎች፣ ህሙማን እና አምቡላንሶች ልዩ ጥበቃ እንዲያገኙ የሚያዝ መሆኑን የጠቀሱት በአማራ ክልል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ፅሀፊ አቶ ታፈረ መላኩ ለዶቼቬሌ  እንደገለፁት

የጤና ተቋማትና  እና ትምህርት ቤቶች በመውደማቸው ሌሎች ደግሞ በሥጋት ምክንያት በመዘጋታቸው 4.7 ሚሊየን ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ተገልጿል በዚህም መስረት 4.870 ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ 5379 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ወድመዋል

መንገድ የለም መንቀሳቀስ አይቻልም አገልግሎት መስጫ  ተቋማት ዝግ ናቸው ሰዎች በየደቂቃው በሚለዋወጠው የአካባቢው  የፅጥታ ስጋት ምክንያት  በፍርሀት  ታስረው ነው ያሉት፣  የጤና ባለሙያዎች ህክምና እየሰጡ ሆስፒታሎች በጥይት ይደበደባሉ ።  ይህም  ሕዝብን የጤና አገልግሎት እንዳያገኝ አድርጎታል።እኛ እያልን ያለነው አለም አቀፍ የስባዊ መብት ህግ ይከበር ፣ ምንም የማያውቁ ሰላማዊ ሰዎች  እልቂት ይቁም ነው  ሲሉ ለ DW የገልፁት የክልሉ የ ጤና ባለሙያ ፕሮፊሰር ፈንቴ አንባው ናቸው ።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮምስል Alemnew Mekonnen/DW

አለም አቀፉ ማህበረስብ እና ሚዳያዎችትኩረት ያላደረጉበት የአማራ ክልል ግጭት ከፖለትካ ነፃ የሆኑት ተቋማት ዋጋ እያሰከፈለ ሲሆን ባለሙያዎችም በመሳሪያ ታጅቦ ህክምና ለመስጠት ይገደዳሉ ፣ በየግዜው መሳሪያ ባነገቡ ሀይሎች  ባለሙያዎች፤  በሚደርስባቸው ጫና ምክንያት በሥራ ገበታቸው ላይ ወጣ ገባ እያሉ ለመሥራት መገደዳቸውን ተገልጿል ክልሉ በአሁኑ ወቅት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ከ48 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል ተብሏል።

 ሐና ደምሴ

ነጋሽ መሐመድ

ፀሐይ ጫኔ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW