1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አማራ ክልል ደቡብ ሜጫ ውስጥ በታጣቂዎች የተገደሉት ሰዎች ጉዳይ

ዓርብ፣ ሐምሌ 19 2016

የአማራ ክልል መንግሥት ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ከተያዙት ሰዎች መካከል ጽንፈኛ ባላቸው ኃይሎች "አራት ሰዎች ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ተገድለዋል" ማለቱ ይታወሳል። የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል የተባለው አካል ግን ድርጊቱን "አሁንም ቢሆን ማን እንደፈጽመው በግልጽ የምናውቀው ነገር የለም"ሲል አስታውቋል።

Grenze Äthiopien Sudan
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል ከሰሞኑ በታጣቂዎች የተገደሉ ሰዎች ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል

This browser does not support the audio element.

ሰሞኑን በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ደቡብ ሜጫ ወረዳ በታጣቂዎች ተይዘው በእንብርክክ እንዲሄዱ ተደርገው ሲቀጡ ከነበሩት አሥራ ስምንት ሰዎች መካከል አራቱ መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የክልሉ መንግሥት አስታውቀዋል።የፌዴራል መንግሥት እና የፋኖ ታጣቂዎች እንዲደራደሩ የማግባባት ሥራ ለማከናወን የ "አመቻችነት" ሚና ይዞ ተቋቋመ የተባለው የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል በተንቀሳቃሽ ምስሉ የሚታየት ሰዎች አባላቱ እንዳልሆኑ ገልጾ ድርጊቱን "ማን እንደፈፀመው ፣ ለምን እንደተፈፀመ በግልጽ የምናውቀው ነገር የለም" ብሏል። ከተገደሉት ሰዎች መካከል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የወረዳው ሀገረ ስብከት ኃላፊ እንደሚገኙበት ተገልጿል።


ስለ ግድያው "የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል" ምን ይላል?

"አሁንም ቢሆን ማን እንደፈፀመው በግልጽ የምናውቀው ነገር የለም። መንግሥት የሰጠው መግለጫ አለ፣ በፋኖ በኩልም መግለጫ እንጠብቃለን። ማን ነው የፈፀመው? ድርጊቱስ ለምንድን ነው የተፈጸመው? የሚለው ማለት ነው። የሰላም ካውንስሉ አባላትም ቢሆኑ የን የሚያስደርግ ሥራ አይደለም የሰላም ካውንስሉ የሚሠራው" 

በአማራ ክልል የኢንተርኔት መቋረጥ ያስከተለዉ መጠነሰፊ ችግር

ይህን ያሉት በአማራ ክልል ጦርነት ውስጥ በገቡት ሁለቱ አካላት [የፌዴራል መንግሥት እና የፋኖ ታጣቂዎች] መካከል ድርድር እንዲደረግ የ"አመቻችነት" ሚና ይዞ ተቋቋመ የተባለው "የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል" የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት እያቸው ተሻለ ናቸው።

ይህ ካውንስል "ድንገት ነው የተቋቋመው" የሚሉት ኃላፊው፣ መከላከያ ሠራዊት አማራ ክልል ውስጥ በስምንት ቀጣናዎች ክልሉ ላይ ያለውን ግጭት እንዴት እናስቁመው? በሚል ያካሄደውን ስብሰባ ተከትሎ በስብሰባው የተሳተፉት ተደራደሩ የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው ለመቋቋማቸው መነሻ መሆኑን ያስታውሳሉ። አመቻች እንጂ ተደራዳሪም አደራዳሪም እንዳልሆኑ፣ ይልቁንም ሁለቱ ወገኖች አደራዳሪ እና ተደራዳሪ እንዲለዩ፣ የሚደራደሩበትንም ቦታ እንዲመርጡ የማግባባት ሥራ በማከናወን ሰላም እንዲሰፍን ለማገዝ በሚል መቋቋማቸውን ገልፀዋል።

ዝርፊያ እና ግድያ በአማራ ክልል
ከተገደሉት መካከል የሃይማኖት መሪዎችም ይገኙበታ


በሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ ለስልጠና ባሕር ዳር ደርሰው ሲመለሱ የነበሩ የተባሉት ሰዎች ላይ ከዚህ የሰላም ካውንስል ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል የተፈፀመው ድርጊት የሃይማኖት መሪዎችን፣ የሀገር ሽማግሌዎችን እና እናቶችን በሕዝብ ፊት በእንብርክክ ያስኬደ ነው። ከእነዚህ ሰዎች መካከል አራቱ የተገደሉ መሆኑን፣ ከመካከላቸውም የወረዳው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ አንዱ እንደነበሩ የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ኃላፊ መልዓከ ምሕረት ግሩም አለነ ለዶቼ ቬለ አረጋግጥዋል።


ስለ ድርጊቱ የክልሉ መንግሥት እና የባለሥልጣናት ምላሽ


የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ከተያዙት ሰዎች መካከል ጽንፈኛ ባላቸው ኃይሎች "አራት ሰዎች ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ተገድለዋል" ማለቱ ይታወሳል። የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል የተባለው አካል ግን ድርጊቱን "አሁንም ቢሆን ማን እንደፈጽመው በግልጽ የምናውቀው ነገር የለም" በማለት አባላቱ ከእነዚህ መካከል እንደሌሉበት አስታውቋል።

የማስለቀቂያ ገንዘብ ህይወቱን ያልታደገው ታጋች - በከሚሴ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሠ ቱሉ በተረጋገጠ የፌስቡክ መገናኛ ዐውታራቸው "የሽፍታ ስብስብ እና የሽብር ቡድን" ያሉት፣ ግን በስም ያልጠቀሱት አካል "ለምን ስለ ሰላም ሰራችሁ ብሎ ንፁሃን የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና እናቶችን ኢ-ሰብዓዊ እና ክብረ-ነክ በሆነ መንገድ ከማወረዱም በላይ በክልሉ ሰላም ይምጣ ስላሉ ብቻ የግፍ እርምጃ ወስዶባቸዋል።" በማለት ጽፈዋል።  በጉዳዩ ላይ ከፋኖ ታጣቂዎች፣ ከሰብዓዊ መብት ድርጅቶች እና ተቋማት ምላሽ እና መብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

በአማራ ክልል የቀጠለው የመከላከያ ሰራዊትና የፋኖ ታጣቂዎች ግጭት

የጭካኔ ድርጊትና የተጠያቂነት አለመኖር

ኢትዮጵያ ውስጥ እገታ፣ በእሳት መቃጠል፣ ሰውን ዘቅዝቆ መሰቀል፣ ሴቶችን መደፈር እና መሰል የጭካኔ ድርጊቶች በተለያዩ ቦታዎች የተፈፀሙ ሲሆን ተጠያቂነት በአግባቡ አልመስፈኑም መሰል የጭካኔ ድርጊቶችን እንዲበራከቱ እያደረገ ይገኛል።

 

ሰለሞን ሙጨ

እሸቴ በቀለ

ፀሐይ ጫኔ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW