አማኑኤል ሆስፒታል ያጋጠመው የቦታ እጥረት
ረቡዕ፣ መጋቢት 18 2016
አዲስ አበባ የሚገኘዉ የቅዱስ አማኑኤል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለታካሚና አካሚዎች በቂ ቦታ እንደሌለዉ ሐኪሞች አስታወቁ።ከቅርብ ግዜ ወዲሕ ቀላል እና መለስተኛ የሚባሉት የአእምሮ ህመም ህክምና በተለያዩ ሐኪም ቤቶች ቢሰጥም አብዛኛዉ የእዕምሮ ሕሙም አሁንም የሚታከመዉ አማኑኤል ሆስፒታል ነዉ።ሆስፒታሉ ከአገልግሎት መስጠት ከጀመረ 80 አመት ሆኖታል።
በኢትዮጵያ እስካሁን የአእምሮ ጤና ፓሊሲ አለመኖሩ በዘርፉ ያለውን ችግር አባብሶታል ዶ/ር ክብሮም ሀይሌ የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት እና የአማኑኤል ሆስፒታል ሚዲካል ዳይሬክተር ለ DW እንደተናገሩት።በአመት 130ሺ ማለት በቀን ከ 350 በላይ የአእምሮ ህመምተኞች ወደ ሆስፒታሉ ይመጣሉ። ሀኪሞቹም በሰአት በአማካይ 44 ህመምተኞችን ያክማሉ ማለት ነዉ።80% የሚሆኑት ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡት ከባድ የአእምሮ ህክምና እና ክትትል የሚይስፈልጋቸው ናቸው ።
ይህ ማለት ነባራዊ ሁኔታዎች መገንዘብ የማይችሉ በእውን የሌሉ ነገሮችን ማየት፣መሰማት፣ እና ዝብርቅርቅ ያሉ ሀሳቦች ማንፀባረቅ የሚታይባቸው ታካሚዎች እንደሆኑ የገለፁት ዶክተር ክብሮም ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት በዚህ በሽታ የተያዙ ሰዎች በመሆናቸው ሰፊና ከተፈጥሮ ጋር የተዋሃደ አካባቢ ይፈልጋሉ። የአእምሮ ህመም በባህሪው ጊዜን የሚፈልግ ነው ለታካሚዎች ሆነ አገልግሎት ለሚሰጡ ባለሞያዎች ከታካሚው ቁጥር ጋር የሚመጣጠን ሰላማዊ የሆነ ሰፊ ባታ ያስፈልጋል ይላሉ ።
እንዲህ በተደራራቢ እና ፋታ በማይሰጥ ስራ በሀገሪቱ በብቸኝነት የሚያገለግለው የቅዱስ አማኑኤል ሆስፒታልየአእምሮ ህክምና ዶክተሮች ለተጨማሪ ትምህርት እና ስልጠና እንዲሰጣቸው ለሚያቀርቡት ጥያቂ የ ሚንስትር መስራቤቱ ምላሽ የዘገየ እንደሆነ ባለሙያው ተናግረዋል።
ሐና ደምሴ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ