1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካን ወቀሳ

ዓርብ፣ ሐምሌ 28 2009

በተመድ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሰደር ኒኪ ሃሊ አፍሪቃ የዓለማችን የረሀብ እና የግጭቶች ማዕከል መሆኗ የመሪዎቿ የጋራ ጥፋት ነው ብለዋል። የሰብዓዊ መብት እና የዓለም አቀፍ ህግ መምህር በበኩላቸው የችግሩ መንስኤ በአፍሪቃ ተጠያቂነት አለመኖሩ መሆኑን ገልጸው የዩናይትድ ስቴትስ መርህ ወጥ አለመሆንም የችግሩ አካል መሆኑን ተናግረዋል።

Hunger im Sahel Bildergalerie Tschad
ምስል Andy Hall/Oxfam

የአፍሪቃ መንግሥታት ተወቀሱ

This browser does not support the audio element.

ከ 14 ሚሊዮን በላይ ዜጎቻቸው ለረሀብ የተጋለጡባቸው የአፍሪቃ መንግሥታት ችግሩን ለመከላከል አስቀድመው ባለመዘጋጀት ተወቀሱ። በተመድ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሰደር ኒኪ ሃሊ በዚህ ሳምንት እንዳሉት አፍሪቃ የዓለማችን የረሀብ እና የግጭቶች ማዕከል መሆኗ የመሪዎቿ የጋራ ጥፋት ነው። አምባሳደሯ የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ በቀጣዮቹ ዓመታት የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ተመልካች መስሪያ ቤት አባል እንድትሆን የአፍሪቃ ሀገራት የሰጡትን ድጋፍም አስገራሚ ብለውታል። በአስተያየቱ ላይ ለዶቼቬለ ማብራሪያ የሰጡ የሰብዓዊ መብት እና የዓለም አቀፍ ህግ መምህር በአፍሪቃ ተጠያቂነት አለመኖሩ የችግሩ መንስኤ መሆኑን ገልጸው የዩናይትድ ስቴትስ መርህም ወጥ አለመሆንም የችግሩ አካል ነው ብለዋል። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW