1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

አሜሪካ ለሜክሲኮ ተገን ጠያቂዎች በርዋን ከፈተች

ዓርብ፣ የካቲት 12 2013

በዩናይትድ ስቴትስ የፍልሰት ፖሊሲ ለውጥ እና መሻሻል ከተደረገ በኋላ የአሜሪካ መንግሥት ከሜክሲኮ ለሚመጡ የጥገኝነት ጠያቂዎች  ድንበር እንዲያቋርጡ በድጋሚ መፈቀድ መጀመሩ ተመለከተ።

USA Mexiko | Migranten beantragen Asyl in El Paso
ምስል Herika Martinez/AFP

በዩናይትድ ስቴትስ የፍልሰት ፖሊሲ ለውጥ እና መሻሻል ከተደረገ በኋላ የአሜሪካ መንግሥት ከሜክሲኮ ለሚመጡ የጥገኝነት ጠያቂዎች  ድንበር እንዲያቋርጡ በድጋሚ መፈቀድ መጀመሩ ተመለከተ። አዲሱ የጥገኝነት ረቂቅ ውሳኔ ከዛሬ ዓርብ ጀምሮ ከሚክሲኮ የሚመጡ የጥገኝነት አመልካቾች ያቀረቡትን ማመልከቻ በፍርድ ቤት  ለመከታተል  ወደ አሜሪካ እንዲገቡና  እንዲከታተሉ ይፈቅዳል። ውሳኔው ከመተላለፉ ቀደም ሲል ተገን ጠያቂዎቹ ተቀባይነት ስለማግኘት አለማግኘታቸው በሀገራቸው ሆነው እንዲከታተሉ የሚደነግግ ብቻ ነበር። አዲሱን የጥገኝነት ማሻሻያ ረቂቅ የዩናይትድ ስቴትስ ዲሞክራቶች ለፕሬዚዳንት ጆ ቢደን ኮንግረስ ውስጥ ለታሰበው የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ረቂቅ  በማስተዋወቃቸው ውሳኔው መተላለፉ ተመልክቷል። ውሳኔው ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸዉ አሜሪካ ውስጥ ለሚኖሩ 11 ሚሊዮን ስደተኞች  የመኖርያ ፈቃድን ለማግኘት መንገድ የሚዘረጋ እንደሆነ ተመልክቷል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW