1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

አሜሪካ ሰሞኑን በተገን ጠያቂዎች ላይ ያሳለፈቻቸው ውሳኔዎች አንድምታ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 23 2018

የአሜሪካ የዜግነት እና የስደተኞች አገልግሎት ለሁሉም የተገን ጥያቄ ውሳኔ መስጠት ማቆሙን ሰሞኑን አስታውቋል።ርምጃው አንድ አፍጋናዊ በዋሽንግተን ዲሲ በብሔራዊ ዘብ አባላት ላይ ተኩስ መክፈቱን ተለትሎ ነው።ከዚህ ውሳኔ ቀደም ብሎ ትራምፕ ከሦስተኛው ዓለም ሀገራት ወደ አሜሪካን የሚሰደዱ ሰዎች በሙሉ በሙሉ እንደሚያስቆሙ ገልፀው ነበር።

ዶናልድ ትራምፕ፤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት
ዶናልድ ትራምፕ፤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንትምስል፦ Alex Brandon/AP Photo/picture alliance

አሜሪካ በተገን ጠያቂዎች ላይ ያሳለፈቻቸው ውሳኔዎች አንድምታ

This browser does not support the audio element.

አሜሪካ፣ዋሽንግተን ዲሲ ከነጩ ቤተ መንግሥት በቅርብ ርቀት ላይ ሁለት የብሔራዊ ዘብ አባላት ባለፈው ሣምንት በጥይት ተመትተው የአንደኛዋ ሕይወት ማለፍን ተከትሎ፣በአሜሪካ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ ላይ በርካታ ለውጥ እንደሚኖር አየተነገረ ነው።  የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዳስታወቁት፣በጥይት ከመቱት የብሔራዊ ዘብ አባላት አንደኛዋ ስትሞት፣ ሁለተኛው ደግሞ በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛል።

ጥቃቱን ተከትሎ ከአፍጋኒስታን የመጡ የሁሉም የስደተኝነት ጥያቄዎች የታገዱ ሲሆን፣በአሜሪካ ያሉ አፍጋኒስታናዊ ዜጎች ተጠርጣሪው አነሱን እንደማይወክል በመግለጽ ውሳኔውን እየተቃወሙ ነው። 

ስዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት ከ19 አገሮች ወደ አሜሪካ ለተሰደዱ ግለሰቦች የተሰጠውን የመኖሪያ እና የሥራ ፈቃድ እንደገና እንደሚመረምር አስታውቋል። ትራምፕ  ከዚህ ውሳኔ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ፣ ከሁሉም "የሦስተኛ ዓለም አገሮች" ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የሚያደርግ "ዘላቂ ዕገዳ" ለመጣል ዕቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል።ይሁንና፣በትናንትናው ዕለት ከመገናኛ ብዙኃን ጋር ቆይታ ያደረጉት የዩናይትድ ስቴትስ የሃገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊ  ክሪስቲ ኖም፣አሜሪካ ከጥቃት፣ከረሃብና ከሌሎች ችግሮች የሚሸሹትን የምትቀበል አገር መሆኗን ገልጸው ዕገዳው የተከማቹ የጥገኝነት ጥያቂዎች ጉዳይ፣ በትራምፕ አስተዳደር ጥብቅ መስፈርት መሰረት እስኪፈተሹ ድረስ የሚቆይ መሆኑን አስታውቀዋል ።

በእነዚህና ተያያዥ የሰሞኑ ጉዳዮች ዙሪያ፣ከአትላንታው ዘጋቢያችን ታሪኩ ኃይሉ ጋር ቆይታ አድርገናል።

ሙሉ ቃለ ምልልሱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

 

ታሪኩ ሐይሉ
ፀሀይ ጫኔ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW