1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አሜሪካ በኢራን ተመተው ከወደቁ አውሮፕላኖች ውስጥ የጠፉ ዜጎቿን ለማግኘት ፍለጋዋን ቀጥላለች

ቅዳሜ፣ መጋቢት 26 2018

ትናንት ዓርብ በኢራን ከተመታው የአሜሪካ F-15E አውሮፕላን ሁለት የበረራ አባላት ውስጥ አንዱ ሲተርፍ ሌላ የጦር አባል የደረሰበት ባለመታወቁ የአሜሪካ ወታደራዊ ፍለጋ እና የማዳን ስራ አሁንም ቀጥሏል።ኢራን፤ የአሜሪካን A-10 የጦር አውሮፕላን መትታ እንደነበርም ገልጻለች።

Niederlande Venlo 2026 | US-Tankflugzeug KC-135 auf dem Weg nach Israel
ምስል፦ Nicolas Economou/NurPhoto/picture alliance

አሜሪካ በኢራን ተመተው ከወደቁ ከሁለት አውሮፕላኖች ውስጥ የጠፉ ዜጎቿን ለማግኘት ፍለጋዋን ቀጥላለች።አርብ ዕለት በኢራን ጦርነት ሁለት የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች በተለያዩ አጋጣሚዎች ተመተው መውደቃቸው ተዘግቧል።በኢራን የተመታው  የአሜሪካ F-15E አውሮፕላን ሁለት የበረራ አባላት ውስጥ አንዱ ሲተርፍ ሌላ የጦር አባል የደረሰበት ባለመታወቁ የአሜሪካ ወታደራዊ ፍለጋ እና የማዳን ስራ አሁንም ቀጥሏል።ኢራን፤ የአሜሪካን A-10 የጦር አውሮፕላን መትታ እንደነበርም ገልጻለች።

በትናንትናው ዕለትም አንድ የዩናትድ ስቴትስ ባለስልጣን ኢራን ዉስጥ አንድ የአሜሪካ ተዋጊ ጄት ተመትቶ መዉደቁን አስታወቀዋል።ሮይተርስ ዜና አገልግሎት ሥማቸዉን ያልጠቀሳቸውን የዩናትድ ስቴትስ ባለሥልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበዉ የአዉሮፕላኑ አብራሪና ባልደረቦቹ በይሕወት መትረፍ አለመትረፋቸዉ አልታወቀም።ሰዎቹን ለማግኘት አሰሳ እየተደረገ መሆኑን ባለሥልጣኑ አስታዉዋል።

የኢራን ጦር ኃይል F 35 የተባለዉን  የዩናይትድ ስቴትስ ዘመናዊ ተዋጊ ጄት መትቶ መጣሉ ቀደም ሲል ተዘግቦ ነበር።የአሜሪካዉ ባለሥልጣን ግን ተመትቶ ሥለወደቀዉ አዉሮፕላን ዓይነት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።የአሜሪካ መከላከያ ሚንስቴርም ሆነ፣ ማዕከላዊ ዕዝ ሥለ አዉሮፕላኑ መመታት አላስታወቁም።እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ ኢራን ላይ ጦርነት ከከፈቱ ወዲሕ የአሜሪካ ተዋጊ ጄት ሲመታ ያሁኑ የመጀመሪያዉ ነበር።እነዚህ ክስተቶች የመጡት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ  ስለኢራን ጦርነት ለህዝባቸው ባደረጉት ብሔራዊ ንግግር አሜሪካ “ኢራንን አሸንፋ ሙሉ በሙሉ አወደመች” ካሉ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው። 

አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የገጠሙት ጦርነት አምስት ሳምንት ያስቆጠረ ሲሆን፤  ኢራን የባህረ ሰላጤውን አካባቢ የኃይል መሠረተ ልማት በማነጣጠር እና በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በኩል የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ጭነቶችን በመቆጣጠር  የአፀፋ ምላሽ  እየሰጠች ትገኛለች። ይህም  በዓለም ዙሪያ  ኢኮኖሚን እያወከ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።

 

ፀሐይ ጫኔ

ዮሀንስ ገብረእግዚአብሄር

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW