1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሜሪካ ኤምባሲዋን በኢየሩሳሌም ከፈተች

ሰኞ፣ ግንቦት 6 2010

በእስራኤል ቴል አቪቭ ከተማ የነበራትን ኤምባሲ ወደ ኢየሩሳሌም ያዘዋወረችው አሜሪካ አዲሱን ኤምባሲዋን ዛሬ በይፋ ከፍታለች፡፡ የአሜሪካንን እርምጃ በመቃወም በእስራኤል እና ጋዛ ድንበር ላይ ከተሰባሰቡ ፍልስጤማውያን ውስጥ በትንሹ 52 ሰዎች ሲገደሉ ከ1500 በላይ ቆስለዋል፡፡

Israel Eröffnung der US-Botschaft in Jerusalem
ምስል Reuters/R. Zvulun

ለተቃውሞ የወጡ በርካታ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል

This browser does not support the audio element.

አሜሪካ አዲሱን ኤምባሲዋን ዛሬ በኢየሩሳሌም በተካሄደ ይፋዊ ስነ ስርዓት ከፍታለች፡፡ በስነ ስርዓቱ ላይ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያምን ኔታንያሁን ጨምሮ በርካታ ባለስልጣናት እና ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል። 

ከወራት በፊት ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ መሆኗን ያጸደቁት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገራቸው ኤምባሲ ከነበረበት ቴልአቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲዛወር ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ የቀድሞ የአሜሪካ መሪዎች በፍልስጤም እና እስራኤል መካከል የሰላም ስምምነት እስኪደረግ በሚል የኤምባሲ ማዛወሩን ሲያዘገዩት ቆይተዋል፡፡ የሰላም ስምምነቱ ምዕራብ ኢየሩሳሌምን ለእስራኤል፣ ምስራቅ እየሩሳሌምን ደግሞ ወደፊት ለሚመሰረተው የፍልስጤም አገር ዋና ከተማነት በማከፋፈል ረዥም ዓመታት የዘለቀውን ደም አፋሳሽ ግጭት ለማስቆም ተስፋ ተጥሎበት ነበር፡፡ 

ምስል Getty Images/AFP/J. Guez

አሜሪካ ለግጭት መንስኤ ሆኖ የቆየው አወዛጋቢው የኢየሩሳሌም ጉዳይ በስምምነት እንዲፈታ የአደራዳሪነት ሚና ይዛ የቆየች ቢሆንም የፕሬዝዳንት ትራምፕ አቋም እና እርምጃ ገለልተኝነቷን ጥያቄ ውስጥ አስገብቶታል፡፡ የአሜሪካንን እርምጃ ተከትሎ ዛሬም ጭምር በተካሄደ ተቃውሞ በርካታ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል፤ ጉዳትም ደርሶባቸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ለተቃውሞ በወጡ ፍልስጤማውያን ላይ እስራኤል በወሰደችው የኃይል እርምጃ በትንሹ 52 ሰዎች ሲገደሉ ከ2000 በላይ ቆስለዋል፡፡ የእስራኤል የኃይል እርምጃ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ከበርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ሀገራት ውግዘት ደርሶበታል፡፡

አሜሪካ ኤምባሲዋን በኢየሩሳሌሙ ስለመክፈቷ በስፍራው ከሚገኘው ወኪላችን ዜናነህ መኮንንን ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።

ዜናነህ መኮንን

ተስፋለም ወልደየስ

ነጋሽ መሐመድ  

  

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW