1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

አሜሪካ ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ ሃገሮች የነደፈችው አዲስ ስትራቴጂ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 4 2014

አሜሪካ ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ ሃገሮች የነደፈችው አዲስ ስትራቴጂ ከኢትዮጵያ ሁኔታ አኳያ ከፍተኛ አንደምታ እንዳለው በአትላንቲክ ካውንስል ከፍተኛ ተመራማሪ ገለጹ። ተመራማሪው አዲሱ የአሜሪካ ስትራቴጂ በአፍሪካውያን ፍላጎትና ፈቃድ ላይ የተመሠረተ መሆኑ፣በሯሷ መንገድና ዐስተሳሰብ ለምትሄደው ኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም አለው ብለዋል።

Südafrika Präsident Cyril Ramaphosa und Blinken
ምስል Andrew Harnik/REUTERS

የአንቶ ብሊንከን ጉዞ ፤ ከኃያላኑ ፍላጎት አንጻር የአፍሪቃውያን አቋም

This browser does not support the audio element.

አሜሪካ ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ ሃገሮች የነደፈችው አዲስ ስትራቴጂ ከኢትዮጵያ ሁኔታ አኳያ ከፍተኛ አንደምታ እንዳለው በአትላንቲክ ካውንስል ከፍተኛ ተመራማሪ ገለጹ።

ከፍተኛ ተመራማሪው አቶ ገብርኤል ንጋቱ፣ለዶይቸ ቨለ እንደገለጹት አዲሱ የአሜሪካ ስትራቴጂ በአፍሪካውያን ፍላጎትና ፈቃድ ላይ የተመሠረተ መሆኑ፣በሯሷ መንገድና ዐስተሳሰብ ለምትሄደው ኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም አለው።

ተመራማሪውን ያነጋገራቸው የአትላንታው ዘጋቢያችን ታሪኩ ኃይሉ ዝርዝሩን አድርሶናል

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፣በአፍሪካ ሃገሮች በቀጠለው ጉብኝታቸው ያስተዋወቁት የዩናይትድስቴትስ ከሰሃራ በታች ለሚገኙ ሃገሮች ያዘጋጀችው አዲስ ስትራቴጂ፣ቅድሚያ የሚሰጣቸው ብሎ በአራት የከፈላቸው የጋራ ጉዳዮች ግልጽነት፣ዴሞክራሲ፣ኮቪድ 19 እና የአየር ንብረት ለውጥ ናቸው።

ምስል REUTERS

ስትራቴጂውን ይፋ ባደረጉበት ንግግራቸው፣ዩናይትድስቴትስ የአፍሪካን ምርጫዎች አትወስንም ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣እነዚህን ምርጫዎች የማድረግ መብት ሌላ የማንም ሳይሆን የአፍሪካውያንና የአፍሪካውያን ብቻ ነው ብለዋል።

ይኸው አዲሱ ስትራቴጂ፣በአፍሪካውያን ፍላጎትና ፈቃድ ላይ የተመሠረተ መሆኑ ለኡትዮጵያ ትርጉም እንዳለው በአሜሪካ የጥናትና ምርምር ማዕከል የሆነው የአትላንቲክ ካውንስል ከፍተኛ ባልደረባ አቶ ገብርኤል ንጋቱ፣ለዶይቸ ቨለ ገልጸዋል።

"ኢትዮጵያ በራሷ መንገድና በራሷ ዐስተሳሰብ የምትሄድ ሃገር ነች።አና ከምሥራቁም ከምዕራቡም ሳይሆን ከሁለቱም የሚጠቅማትን የምትወስድ ሃገር ናት እና ለኢትዮጵያ ትልቅ አንደምታ አለው።"

ብሊንከን፣ዴሞክራሲና ዲፕሎማሲ ላይ ባተኮረው ገለጻቸው፣ሁከትን ለማስቆምና የሠላም ጎዳና ለመክፈት አሜሪካ ከአፍሪካ መሪዎች፣ቀጣናዊ ድርጅቶችና ዜጎች ጋር መስራቷን እንደምትቀጥል ሲናገሩ፣ከጠቀሷቸው ሃገሮች መኻከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት።

"በእነዚህ ጥረቶች፣የአፍሪካ ሃገሮች የአሜሪካን ድጋፍ ሊተማመኑ ይችላሉ።ለዚህም በዚህ ሣምንት የጉብኝቴ ቁልፍ ትኩረት በሆነውና እንደ ቻድ፣ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ምሥራቃዊ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ በምናደርገው ተሣትፎ አሳይተናል።"

ይህንኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን የትኩረት አቅጣጫ አስመልክተው፣አቶ ገብርኤል ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

ምስል REUTERS

"ዴሞክራሲና ሰላምን አሰመልክቶ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪቃ የሠላም ማማ ነች።በዴሞክራሲና ሠላምና ማምጣት የሚለው የታየ ነው ፤አርሱ ግን በንግግሩም ላይ  ቻድ፣ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ምስራቃዊ ኮንጎ በዚህ ጉብኝቴ ላይ ቅድሚያ ሰጥቻቸው የምናያቸው ሃገሮች ነው ብሏል።"

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣አፍሪካ ለምን ተፈላጊ አህጉር እንደሆነች ባመላከተው የስትራቴጂ ሰነዱ ክፍል፣በ2050 በዐለም ላይ ከአራቱ ሰዎች አንዱ፣አፍሪካዊ እንደሚሆን ጠቁመዋል።እነዚህም የዓለምን ዕጣ ፈንታም ይቀርጻሉ ብለዋል።

የብሊንከን የአፍሪካ  ጉብኝት፣ የሩሲው አቻቸውን ተመሳሳይ ተልዕኮ ተከትሎ የሚካሄድ ሲሆን፣በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች ሊከተሉት የሚገባው የሠላምና የገለልተኝነት አቋም ሊሆን እንደሚገባው የአትላንቲክ ካውንስል ከፍተኛ ተመራማሪው አመልክተዋል።

"ራሽያ ዩክሬንን በመውረሯ፣ይሄ ዓላማችን እየተሳካ አይደለምብሎ ደጋግሞ ይናገራል።አና ይሄ ምንድን ነው የሚያሳየው፣በእጅ አዙር የአፍሪካውያንን ዕጅ ጠምዝዞ ወደ አሜሪካ ፖሊሲ እንደሚጡ ራሺያን እንዲያወግዙ በሚሰሩት ሥራ ዩክሬንን መውረራቸው ስህተት ነው፣በዚያ የተነሳ የሦስተኛው የዓለም ሃገራት የሚያስፈልግ የሰብዓዊ ዕርዳታ፣እህል መድኃኒትእንዳይመጣ እያደረገ ነው፤የነፍስ አድን ዕርዳታ እንዳይመጣ እያደረጉ ነውና በተዘዋዋሪ አውግዟቸው የሚል ነውና እኛ አፍሪካውያኖች አቋም በመጠበቅ የገለልተኝነትና የሰላም መፈለግ የኢትዮጵያ መንግስት አቋም እኛ የምንፈልገው በግራም በቀኝም በሩሲያም በዩክሬንም ሠላም ነው የምንፈልገው የሚለውን አቋም ይዞ መቀጠል ያስፈልጋል እንጂ አዎን እከሌ ነው ያደረገው ማወገዝ አለበት የሚለውን ኢንዶርስ(መደገፍ)የለበትም።"ብለዋል።

ታሪኩ ኃይሉ

ምስል Andrew Harnik/AP Photo/picture alliance

ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW