1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አምስት ሺ ሩሲያ ሰራሽ መኪኖች፣ ኢትዮጵያ ሊገቡ ነው

ሰኞ፣ የካቲት 24 2017

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን የሀገሪቱን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያዘምኑና ተወዳዳሪነትን የሚያሳድጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሽከርካሪዎችን ከሩሲያ ለማስመጣት ማቀዱን አስታወቀ፡፡ የፌደሬሽኑ ፕረዝደንት መኪኖቹ በብድር እንደሚገዙ ገልፀዋል። በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽንምስል፦ Ethiopian Transport Employers Federation

አምስት ሺ ሩሲያ ሰራሽ መኪኖች፣ ኢትዮጵያ ሊገቡ ነው

This browser does not support the audio element.

አምስት ሺ ሩሲያ ሰራሽ መኪኖች፣ ኢትዮጵያ ሊገቡ ነው 

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን የሀገሪቱን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያዘምኑ እና ተወዳዳሪነትን የሚያሳድጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሽከርካሪዎችን ከሩሲያ ለማስመጣት ማቀዱን አስታወቀ፡፡ የፌደሬሽኑ ፕረዝደንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ዛሬ ለዶቸቬለ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ፣ መኪኖቹ በብድር እንደሚገዙ ገልፀው፣ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡም ተናግረዋል፡፡ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ምን ያህል ምቹ ናት?

ኢትዮጵያ በቀጠናው ካሉ ህገሮች ጋር የሚኖርትርን  የንግድ እና የገበያ ትስስር ላማሳደግ እና ላማቀላጠፍ አሁን ያለውን ሀገር አቁዋራጭ  የተሽከርካሪ ገልግሎት ማሻሻል እና ማዘመን አስፍላጊ ነው ያሉት የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን  ፕረዝደንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ፤ ለዚሀም አምስት ሺህ የሚሆኒ  ሩሲያ ሰራሽ መኪኖችን እናስገባለን ብለዋል።

የተሸከርካሪዎቹ የግዢ ሒደት፣ ከሩስያ አምራቾች ድረጀት ጋር በጥምረት  ከሚሰራ ባዝራ ኢትዮጵያ ከተሰኘ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ድርጅትጋር በመተባበር እየተከናወነ መሆኑን የተናገሩት አቶ ብርሃኔ፣ በጉዳዩ ዙርያ ከድርጅቱ ጋር ለአንድ አመት ተኩል ውይይቶችን ስናሂድ ቆይተናል ብለዋል። አሁን ግዢውን ለመፈፀም የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሳቸውን ተናግረው ፡ ከሩሲያ የሚገዙት ተሽከርካሪዎች ፣ የኢትዮጵያን መልክ ዓምድር ታሳቢ ያደረጉ ናቸው ተብሏል።«የኮቴ ክፍያ» ያስመረራቸው የከባድ መኪና ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች

ኢትዮጵያ በቅርቡ፣ ሩሲያና ቻይና የሚገኙበት፣ ብሪክስ በመባል የሚታወቀውን ጥምረት የተቀላቀለች ስትሆን፣ይኸው አባልነት ለዚህ ስራ ማገዙን አቶ ብርሃኔ ገልፀዋል፡፡ ከሩሲያ የሚገቡት መኪኖች የደረቅ፣ የፈሳሽ ጭነት እና የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች መሆናቸውን እና መኪኖቹ ወደ ሀገር ከገቡ በኋላ ኮምቦልቻ በሚገኝ የባዝራ ኢትዮጵያ መገጣጠሚያ ማዕከል ተገጣጥመው ወደ ስራ እንደሚገቡ ተነግሮዋል።

አዲስ አበባ ከተማ ምስል፦ Solomon Muchie/DW

የተሻላ ቲክኖሎጂ ያላቸው ነዳጅ ቆጣቢ ከአየር ብክት ነጻ  የሆኑ እና እረጅም መንገድ የሚጉዋዙ እና በዘርፉ ተወዳዳሪ የሚያደርጉን ናቸው የተባሉትን ተሽከርካሪዎች ለማስገባት አስፈላጊ ሒደቶች ሁሉ ታልፈው፣ የመኪኖቹን የግዢ የምናዝበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ያሉት አቶ ብርሀኔ  መኪኖች ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ  ባየጠቅሱም ተሽከርካሪዎቹ የሚገቡት  በባንክ ብድር እንደሚሆን ተናግረዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለማናገር በተዳጋጋሚ ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም። 

ሃና ደምሴ

አዜብ ታደሰ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW