1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ሆነው ተሰየሙ።

ሐሙስ፣ ጥቅምት 15 2011

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች እንደራሴዎች ዛሬ ባካሄደው 2ኛ ልዩ ስብሰባ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሷ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት አድርጎ መረጠ። አምባሳደር ሳህለወርቅ በተመድ ምክትል i,ዋና ጸሀፊ  አንቶኒዮ ጉቴሬሽ የአፍሪቃ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ተሾመው በማገልገል ላይ ነበሩ።

Äthiopien Sahle-Work Zewde 2014
ምስል፦ Getty Images/AFP/E. Piermont

የአምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ መሾም

This browser does not support the audio element.

አምባሳደር ሳህለወርቅ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣናቸውን የለቀቁትን ፕሬዚደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመን ይተካሉ።ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ሀላፊነታቸውን የለቀቁት የስራ መልቀቂያቸውን  ዛሬ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ስብሰባ ላይ በማቅረብ ነው ። የሀገሪቱ የመጀመሪያ ሴት ፕሬዚደንት ሆነው የተመረጡት ፣ በዲፕሎማትነት ሰፊ የስራ ልማድ ያላቸውአምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በተለያዩ ሀገራት አምባሳደር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፣ ከጎርጎሪዮሳዊው 1989 እስከ 1993 በሴኔጋል የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ እንዲሁም፣ ከ1993 እስከ 2002 በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር እና በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት፣ኢጋድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ በመሆን ሰርተዋል።  አምባሳደር ሳህለወርቅ ሁሉንም ወገኖች በማቀራረብ ባለፉት ወራት በሀገሪቱ የታዩትን ብሔር ተኮር ግጭቶች ለማብቃት እና ሰላም ለማውረድ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ምስል፦ Getty Images/AFP/E. Soteras

የመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው ሊያበቃ አንድ ዓመት ሲቀረው ስልጣናቸውን የለቀቁት ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በርእሰ ብሄርነት ያገለገሉባቸው ያለፉት አምስት ዓመታት በህይወት ጉዟቸው ትልቅ ቦታ የሚይዝ መሆኑን መልቀቂያቸውን ለምክር ቤቶቹ ባቀረቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW