1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አረና ትግራይ የፕሪቶሪያ ስምምነት በአስቸኳይ ይተግበር አለ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 23 2015

ትግራይ ክልል በኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት እንዲኖራት እንደሚታገል ተቃዋሚው ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ ዐስታወቀ። ዓረና ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፦ የኢትዮጵያ ሕገመንግሥትን በማሻሻል አዲስ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ውል ለመመስረት ከሌሎች በኢትዮጵያ ካሉ የፖለቲካ ፖርቲዎች ጋር በጋራ እንደሚሠራ ገልጿል።

የዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ ስብሰባ ተካፋዮች በከፊል ።
ዓረና ትግራይ የቀድሞ የትግራይ ርእሰ መስተዳድር እና የፖርቲው መስራች አቶ ገብሩ አስራትን ጨምሮ 11 አባላት ያሉት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንዲሁም ታዋቂዋ ሴት ፖለቲከኛ ወይዘሮ አረጋሽ አዳነ ጨምሮ 25 የማእከላይ ኮሚቴ አባላት መምረጡንም አስታውቋል ። የዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ ስብሰባ ተካፋዮች በከፊል ።ምስል Million Haileselassie/DW

ፓርቲው ይህን ያለው ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው

This browser does not support the audio element.

ትግራይ ክልል በኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት እንዲኖራት እንደሚታገል ተቃዋሚው ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ ዐስታወቀ። ዓረና ለቀናት ካደረገው የፖርቲው ጉባኤ በኋላ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፦ የኢትዮጵያ ሕገመንግሥትን በማሻሻል አዲስ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ውል ለመመስረት ከሌሎች በኢትዮጵያ ካሉ የፖለቲካ ፖርቲዎች ጋር በጋራ እንደሚሠራ ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ ዓረና ፓርሪ የፕሪቶርያው ውል አፈፃፀም አመርቂ አይደለም ብሏል ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፦ ሦስት የትግራይ ክልል የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በህዝቡ ላይ ይደርሳል ያሉትን በደል በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ዐስታውቀዋል ። በትግራይ ክልል ስልጣን የያዙ ግለሰቦች በተለይም ሴቶችን መግደል፣ ሀብት መውረስን ጨምሮ በተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት ተሰማርተዋል ብለዋል ። ፓርቲዎቹ   የማዕድናት እና የሰዎች ሕገወጥ ዝውውር ላይ ከፍተኛ የፖለቲካ እና ወታደራዊ መሪዎች እጃቸው አለበትሉም አክለዋል። 

በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2000 ዓመተ ምህረት በትግራይ ክልል የመጀመርያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ በመሆን፥ በቀድሞ የሕወሓት ከፍተኛ አመራር እና ሌሎች የተመሰረተውዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ ካለፈው ቅዳሜ ነሐሴ 20 ጀምሮ 5ተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በመቐለ ከተማ አድርጓል። 

«አዲስ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ውል ለመተግበር እንታገላለን» በሚል መሪ ሀሳብ ጉባኤውን ያደረገው ዓረና ፓርቲ ትግራይ ክልል ከጦርነቱ በኋላ ቀድሞ የነበረው የፖለቲካ መርኃ ግብሩን በመለወጥ አዳዲስ የትግል ሀሳቦች ይዞ መቅረቡ እና ትግራይ ክልል በኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በህዝብ ቁጥር መሰረት ከሚኖራት ውክልና በተጨማሪ የሕገመንግስት ማሻሻያ በማድረግ በፌዴሬሽን ምክርቤት ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት እንዲኖራት እንደሚታገል አስታውቋል። 

ትግራይ ክልል በኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት እንዲኖራት እንደሚታገል ተቃዋሚው ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ ዐስታወቀ። ዓረና ለቀናት ካደረገው የፖርቲው ጉባኤ በኋላ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንኑ ዐስታውቋል ።ምስል Million Haileselassie/DW

አዲሱ የዓረና ትግራይ ሊቀመንበር ሆነው በፓርቲው የተመረጡት አቶ ዓምዶም ገብረሥላሴ ትግራይ ክልልን ጨምሮ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ወይም ቬቶ ፓወር እንዲኖራቸው ማድረግ ለሀገሪቱ ሰላም እና ለፌደሬሽኑ ዘላቂነት አስፈላጊ መሆኑ ዓረና ትግራይ መግባባት ላይ መድረሱ ተናግረዋል።

በጦርነቱ ወቅት ሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች የዓረና ትግራይ የሰላም ጥሪን የሚሰሙበት ሁኔታ አልነበረም በማለት የወቀሰው ዓረና ትግራይ ለሉዓላዊነት እና ዴሞክራሲ፥ ከደም አፋሳሹ ጦርነት በኋላ ጦርነቱን ያስቆመ የፕሪቶርያው የሰላም ውል መደረጉን እንደሚደግፍ፤  የእስካሁን አፈፃፀም ግን አመርቂ አለመሆኑ ገልጿል።

ከሰላም ስምምነቱ ዐሥር ወራት በኋላም ትግራይ በአስከፊ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግር ላይ መሆንዋ ያነሳ ፓርቲው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች አሁንም ወደቀዬአቸው አልተመለሱም፣ ፍትህ በማረጋገጥ ወንጀለኞች ለሕግ በማቅረብ አልተሰራም፣ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት አልተከበረም በማለት ግምገማው አስቀምጧል።

የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ ካሕሳይ ዘገየ ተመላሽ የቀድሞ ተዋጊዎች ከማቋቋም ጀምሮ የህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄዎች የመመለስ ስራ በውሉ መሰረት እየተፈፀመ እንዳልሆነ ያነሳሉ።

ዓረና ትግራይ የቀድሞ የትግራይ ርእሰ መስተዳድር እና የፖርቲው መስራች አቶ ገብሩ አስራትን ጨምሮ 11 አባላት ያሉት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንዲሁም ታዋቂዋ ሴት ፖለቲከኛ ወይዘሮ አረጋሽ አዳነ ጨምሮ 25 የማእከላይ ኮሚቴ አባላት መምረጡም አስታውቋል። 

ዓረና ትግራይ የቀድሞ የትግራይ ርእሰ መስተዳድር እና የፖርቲው መስራች አቶ ገብሩ አስራትን ጨምሮ 11 አባላት ያሉት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንዲሁም ታዋቂዋ ሴት ፖለቲከኛ ወይዘሮ አረጋሽ አዳነ ጨምሮ 25 የማእከላይ ኮሚቴ አባላት መምረጡንም አስታውቋል ። የዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ ስብሰባ ተካፋዮች በከፊል ።ምስል Million Haileselassie/DW

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ በጋራ መግለጫ የሰጡት የትግራይ ነፃነት ፓርቲ፣ ሳልሳይ ወያነትግራይ እና የታላቋ ትግራይ ብሄራዊ ሸንጎ የተባሉ ሦስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች፥ ምላሽ ያላገኙ የትግራይ ህዝብ ወቅታዊ ችግሮች በመያዝ ከጳጉሜ 2 ጨምሮ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። 

በትግራይ ስልጣን የያዙ ግለሰቦች ሰዎች በተለይም ሴቶች መግደል፣ ሀብት በመውረር ጨምሮ በተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት ተሰማርተው፣ የማዕድናት እና የሰዎች ሕገወጥ ዝውውር ላይ ከፍተኛ የፖለቲካ እና ወታደራዊ መሪዎች እጃቸው አለበት ያሉት እነዚህ ፓርቲዎች ይህ ወደባሰ ሁኔታ ሳይሻገር ትኩረት እንዲያገኝ በሰልፍ ጥሪ ልናቀርብ ነው ብለዋል። 

የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ደጀን መዝገቦ «የትም አይደርስም በሚል ትእቢት መልስ ያጣው የህዝባችን ጥያቄዎች ይዘን፣ እየተደፈሩ እየተሰቃዩ እየተገደሉ ያሉ ሴት እህቶቻችን፣ በየመንገዱ በዘራፊዎች እየተነጠቀ ያለው ህዝባች፣ ርቦናል የሚል ጥያቄ ያለቸው የታጋይ ወንድሞቻችን ድምፅ ለማሰማት ፥ ለውጥ የግድ መምጣት አለበት ብለን፣ ሶስታችን ፓርቲዎች የጋራ ኪዳን ፈጥረን ሰልፍ ጠርተናል። ወደዚህ ሰልፍ ሁሉም የየራሱ የሚመለከተው ጥያቄ ይዞ እንዲቀላቀል ጥሪ እናቀርባለን» ብለዋል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW