አራተኛዉ ዙር የዓባይ ግድብ ጉባዔ በአዲስ አበባ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 29 2012
ማስታወቂያ
በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ በግብጽ፤ ሱዳን እና ኢትዮጵያ መካከል የሚደረገው አራተኛ ዙር የሦስትዮሽ ስብሰባ አዲስ አበባ ውስጥ በዝግ ተጀምሯል። የመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ብቻ ለአጭር ጊዜ ለመገናኛ ብዙኃን ክፍት ከሆነ በኋላ ነዉ፤ የከፍተኛ ልዑካኑ ጉባኤ በዝግ የጀመረዉ። በነገው ዕለት ማምሻው ላይ ስለዝግ ስብሰባው መግለጫ እንደሚሰጥም ከአዘጋጆቹ ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ፤ ግብጽ እና ሱዳን በሕዳሴው ግድብ የውኃ አሞላል እና መጠን ጉዳይ እስካሁን በተጨባጭ ከስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም። የሦስቱ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚንሥትሮች በሦስት ዙር ለመወያየት ባለፈው ዩናይትድ ስቴትስ ተገናኝተው የተነጋገሩ ሲኾን፤ ግብጽ አዲስ አበባ እና ሱዳን ውስጥ ከዚያ በኋላ መወያየታቸዉ ይታወሳል። በዛሬው ስብሰባ ላይ ሃገራቱ የየራሳቸውን አቋም ይዘው እንደቀረቡ ተገልጧል። በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ