1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አራተኛ ቀኑን የያዘው የሕወሓት ጉባኤ እና የተቃዋሚዎች መግለጫ

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 11 2016

ከህወሓት ጉባኤ ራሳቸውን ያገለሉ ወደ መድረኩ እንዲመለሱ የህወሓት ጉባኤ ጥሪ ማቅረቡን የፓርቲው ቃልአ ቀባይ ገልፀዋል።በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፥ በበኩላቸው ፌደራሉ መንግስት በኩል ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አንድ አድርጎ የመመልከት እንዲሁም በህወሓት ምክንያት ትግራይን የመጉዳት አባዜ መቀጠሉ እንዳሳሳባቸው አስታውቀዋል።

የፓርቲው ጉባኤ እስካሁን በተለያዩ አጀንዳዎች ዙርያ መወያየቱን እና ውሳኔዎች ማስተላለፉን አስታውቀዋል።
14ተኛ ጉባኤ ዙርያ ዛሬ ማብራርያ የሰጡት፥ የጉባኤው ቃል አቀባይ ተደርገው የተሾሙት አቶ አማኑኤል አሰፋ፥ የፓርቲው ጉባኤ እስካሁን በተለያዩ አጀንዳዎች ዙርያ መወያየቱን እና ውሳኔዎች ማስተላለፉን አስታውቀዋል። ምስል Million Haileselassie/DW

አራተኛ ቀኑን የያዘው የሕወሓት ጉባኤ እና የተቃዋሚዎች መግለጫ

This browser does not support the audio element.

 

ከህወሓት ጉባኤ ራሳቸው ያገለሉ አካላት ወደመድረኩ እንዲመለሱ የህወሓት ጉባኤ ጥሪ አቀረበ። የህወሓት ጉባኤ ቃልአቀባይ አቶ አማኑኤል አሰፋ ዛሬ አራተኛ ቀኑ በያዘው ጉባኤ ላይ በሰጡት መግለጫ ራሳቸውን ከጉባኤ ያገለሉ አካላት ሐሳባቸው እንዲገልፁ ጥሪ እንዲደረግላቸው መወሰኑን ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፥ በፌደራሉ መንግስት በኩል ህወሓት እና የትግራይ ህዝብ አንድ አድርጎ የመመልከት እንዲሁም በህወሓት ምክንያት ትግራይን የመጉዳት አባዜ መቀጠሉ እንዳሳሳባቸው አስታውቀዋል።

ከተጀመረ አራተኛ ቀኑ በያዘው የህወሓት 14ተኛ ጉባኤ ዙርያ ዛሬ ማብራርያ የሰጡት፥ የጉባኤው ቃል አቀባይ ተደርገው የተሾሙት አቶ አማኑኤል አሰፋ፥ የፓርቲው ጉባኤ እስካሁን በተለያዩ አጀንዳዎች ዙርያ መወያየቱን እና ውሳኔዎች ማስተላለፉን አስታውቀዋል። በጉባኤው ውስጥ ጉባኤው እንዲራዘም የተነሳ አጀንዳ እንደነበረ የገለፁት ቃልአቀባዩ፥ ይህ ሐሳብ በተለያዩ ምክንያቶች ተቀባይነት አለማግኘቱን ተናግረዋል። በጉባኤው መሳተፍ ይገባቸው የነበረ በተለይም ከደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞን የተወከሉ የፓርቲው አባላት ወደጉባኤው እንዳይመጡ፣ እንዳይሳተፉ፥ በአስተዳደር አካላት ዓፈና መፈፀሙን የገለፁት ቃልአቀባዩ አቶ አማኑኤል፥ ከነዚህ አካባቢዎች በታዛቢነት ለመሳተፍ የመጡ ተሳታፊዎች የተፈጠረውን ክፍተት ለሞምላት በድምፅ እንዲሳተፉ ጉባኤው መወሰኑን አንስተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ቃልአቀባዩ፥ በራሳቸው ፍቃድ ከጉባኤው ውጭ የሆኑ አካላት ወደመድረኩ እንዲመለሱ ጥሪ እንዲደረግ መወሰኑም ገልፀዋል።

14ተኛ ጉባኤ ዙርያ ዛሬ ማብራርያ የሰጡት፥ የጉባኤው ቃል አቀባይ ተደርገው የተሾሙት አቶ አማኑኤል አሰፋ፥ የፓርቲው ጉባኤ እስካሁን በተለያዩ አጀንዳዎች ዙርያ መወያየቱን እና ውሳኔዎች ማስተላለፉን አስታውቀዋል። ምስል Million Haileselassie/DW

በጉባኤው ማጠናቀቅያ አዲስ የህወሓት አመራር ሊመረጥ እንደሚጠበቅ ተነግሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ዛሬ በመቐለ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የትግራይ ነፃነት ፓርቲ፣ የታላቋ ትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ ባይቶና እንዲሁም ሳልሳይ ወያነ ትግራይ በበኩላቸው ወቅታዊ የህወሓት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እና የፌደራል መንግስትና የተቋማቱ ምላሽ የትግራይ ህዝቡን ለስጋት የዳረገ ሲሉ ገልፀውታል። የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ደጀን መዝገበ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ፓርቲና ህዝብ አለመለየት፣ በህወሓት እርምጃ የትግራይ ህዝብን ለመቅጣት የመሞከር አዝማሚያ እየታየ መቀጠሉን አንስተዋል።

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወቅታዊ የህወሓት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እና የፌደራል መንግስትና የተቋማቱ ምላሽ የትግራይ ህዝቡን ለስጋት የዳረገ ሲሉ ገልፀውታል።ምስል Million Haileselassie/DW

ሌላው ሐሳባቸውን የገለፁት የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሃይሉ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ መንግስት እና ዓለምአቀፍ ተቋማት ጨምሮ ሌሎች ብቸኛ የትግራይ ፖለቲካዊ ተወካይ ህወሓት ብቻ አድርጎ መመልከት ለበርካታ ችግሮች መነሻ እየሆነ እንዳለ ገልፀው ይህ እንዲታረም ጥሪ አቅርበዋል።

ሶስቱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፕሪቶርያው ስምምነት እንደተጠቀሰው በትግራይ ሁሉም ሐይል አካታች አስተዳደር ሊመሰት ይገባል ብለዋል።

 

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ሚሊዮን ሀይለስላሴ
ሂሩት መለሰ
ፀሐይ ጫኔ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW