አሳሳቢዉ የአዲስ አበባ ቅርስ ይዞታ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 14 2006 እንድያም ሆኖ 105 ኛ ዓመትን ያከበረችዉ የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ዛሪ በዘመናዊ ህንጻና በመንገድ ሥራ ግንባታ ታሪካዊ ቅርሶችዋ እየጠፉ፤ መሆናቸዉን የቅርስ ተቆርቋሪ ባለሞያዎች ይናገራሉ። አዲስ አበባ ከተማን ለማልማት በሚደረገዉ ሥራ ጥንታዊና ታሪካዊ ህንጻዎች እንዳይፈርሱ ምን እየተደረገ ነዉ? አዲስ አበባ ከተማን ለማሻሻል በሚደረገዉ ጥረት ጥንታዊ የቅርስ ይዘቶች እንዳይወድሙ ከቅርስ ጥናት ጥበቃ ባለስልጣን ጋር እየሰራን ነዉ ያሉን የኢትዮጵያ ቅርስ ባላደራ ማህበር ሊቀመንበር አቶ ጌቸዉ ታየ እንደሚሉት፤ ባለማወቅም ሆነ በማወቅ በርካታ ቅርሶች ጠፍተዋል፤ የቀሩትን መጠበቅ ይገባናል
የአዲስ አበባ ከተማ መሰረተ ልማት ለማሻሻል በሚደረገዉ ግንባታ ታሪካዊ ቅርሶች እየጠፉ መሆናቸዉን በርካቶች ይናገራሉ። ለታሪካችን ተቆርቋሪ እንደሆንን የምንታወቅ ኢትዮጵያዉያን ቅርስ ጥበቃ ላይ ብዙም ስንሰራ አይታይም የሚሉት የምህንድስና ባለሞያዉ እና የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህሩ አቶ ፋሲል ጊዮርጊስ እንደሚሉት፤
ኢትዮጵያን ፖየትሪ በሚል በፊስቡክ የግጥም ፀሃፊዎችን ያሰባሰቡትና በዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሳምሶን ደምሴ ተፈራ የሰንጋ ተራን መፍረስ አይተዉ ግጥም ጽፈዋል፤ ቢሆንም ይላሉ፤ ለልማት ሲባል በሚደረገዉ ጥረት መፍረስ የለበትም አልልም ይላሉ
እንደ ገጣሚ ሳምሶን ደምሴ ሁሉ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህሩ አቶ ፋሲል ጊዮርጊስ፤ ለልማት በሚደረገዉ ሥራ ላይ ተቃዉሞ እንደሌላቸዉ ይገልጻሉ፤ ሆኖም ግን በአዲስ አበባ ከተማ ከመፍረስ የዳኑትን ታሪካዊ ቦታዎች በጋራ መጠበቅ ይገባናል።
መሰረተ ልማትን በመዘርጋቱ ጥረት ቅርስን የመጠበቅ ሃላፊነት ሊዘነጋ አይገባም ያሉንን ባለሞያዎች ለሰጡን ቃለምልልስ እያመሰገንን፤ ሙሉዉን ቅንብር እንዲያደምጡ እንጋብዛለን።
አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ