አሳሳቢዉ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ
ዓርብ፣ መስከረም 11 2016![የሰብዓዊ መብት ኮሚሽn ስዊዘርላንድ ጄኔቫ](https://static.dw.com/image/66196174_800.webp)
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግስት በሃገሪቱ የሚታየዉን ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ መብትጥሰቶች ፤ መሳደዶች ፤ ወከባ እና ግድያን የማያስቆመ ከሆነ የመንግሥታቱ ድርጅት ጠንከር ወዳለ ጫና እና ማዕቀቦች መሄዱ የማይቀር መሆኑ ተገለፀ። የኢትዮጵያ ወቅታዊ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይን ተከትሎ ትናንት ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ላይ የተሰበሰበዉ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ፤የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ በእጅጉ ማሽቆልቆሉ እንዳሳሰበዉ ገልጿል። በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የአውሮጳ የህግ እና የፍትህ ማእከል ተወካይ በበኩላቸዉ በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን የጅምላ ግድያ እና እስር፤ እንዲሁም የተለያዩ ጥቃቶች በዝርዝር ተናግረዋል። ስብሰባዉን በመካፈል ላይ ያሉት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፤ እንደተናገሩት ኮሚሽኑ የሰጠዉን ምክረ ሃሳብ የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያጤነዉ ይገባል።
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ