1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሳሳቢዉ የእስረኞች የስቃይ አያያዝ

እሑድ፣ ኅዳር 24 2010

የተ.መ.ድ. በጠቅላላ ጉባኤ ባፀደቀዉ እና አባል ሃገራቱ የተቀበሉት መሠረታዊ የእስረኞች አያያዝ ስምምነት ሁሉም እስረኞች ተገቢዉ ክብር እንዲሰጣቸዉ፤ የሰብዓዊ መብት እሴትም እንዲከበርላቸዉ ይደነግጋል። እስረኞች ላይ ቁም ስቅምና ጭካኔ የተሞላበት ወይም የሚያዋርዱ አያያዞች ብሎም ቅጣቆችን መፈፀምም ድንጋጌዉ በአፅንኦት ይከለክላል።

Burundi, Symbolbild Folter
ምስል picture-alliance/AP Photo/J. Delay

የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ አለመከበሩም ሌላዉ መነጋገሪያ ነዉ፤

This browser does not support the audio element.

ይህን ሕግ ተቀብለዉ ከፈረሙ ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት። ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በይፋ የሚሰማዉ የሀገሪቱ የአስረኞች አያያዝ አሳሳቢ እና አነጋጋሪ ሆኗል። እስር ቤት ዉስጥ ስቃት የሚፈፀምባቸዉ፤ በአያያዛቸዉ ምክንያትም ለሕልፈተ ሕይወት ብሎም ለአካል ጉዳት እና ሕመም የተዳረጉ የመኖራቸዉ አቤቱታ የፍርድ ቤት ችሎቶች በየጊዜዉ የሚሰሙት መሆኑም እየተዘገበ ነዉ። አቤቱታ ሰሚዉ ፍርድ ቤት የሚሰጠዉ ትዕዛዝ ተግባራዊ አለመሆኑም ሌላዉ ጥያቄ ያስነሳ ጉዳይ ሆኗል። ዶቼ ቬለ አሳሳቢዉን የእስረኞች የስቃይ አያያዝ ሁኔታ የቃኘ ዉይይት አካሂዷል።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW