1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሳሳቢ እየሆነ የሄደው የፕረስ ነጻነት ይዞታ በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ግንቦት 6 2015

ከበርካታ ዓመታት ዓለም አቀፍ ትችትና ውግዘት ወጥቶ የዛሬ አምስት ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ የፕረስ ነጻነት ይዞታው ቀን ወጣለት ተብሎ ነበር። በአሸባሪነት ሳይቀር ተከሰውና እስራት ተፈርዶባቸው የነበሩ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ድንገት ነጻ ተለቅቀው እስር ቤቱ ጋዜጠኛ አልቦም ቀርቶ ነበር።

Symbolbild Exil-Journalismus/Schutz von gefährdeten Journalist*innen | Belarus
ምስል Aleksander Kalka/ZUMA Wire/picture alliance

አሳሳቢ እየሆነ የሄደው የፕረስ ነጻነት ይዞታ በኢትዮጵያ

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ ውስጥ የፕረስ ነጻነት ይዞታ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ትችት ለተወሰኑ ዓመታት እፎይታ አግኝቶ ከሰነበተ በኋላ ዳግም በአሳሳቢነት ይጠቀስ ጀምሯል። አንድ ወቅት ወህኒ ቤቶች ከጋዜጠኛ እስረኛ ነጻ እንዳልሆኑ አሁን በርካታ ጋዜጠኞች በይፋ በሚታወቁም ሆነ ባልታወቁ እስር ቤት እንደሚገኙ እየተገለጸ ነው። የዘንድሮው የፕረስ ነጻነት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲታሰብ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ባለፈው ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ብቻ 29 ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ታስረዋል። መንግሥት ፕረስን በተመለከተ ጥሩ ጥሩ ሕጎችን መደንገጉን የሚገልጹ ወገኖች በጋዜጠኞች ላይ ለሚደርሰው ችግር የሕጉ ተግባራዊ አለመሆን ዋነኛ መንስኤ እንደሆነ ያመለክታሉ።

ዶቼ ቬለ «በኢትዮጵያ አሳሳቢ እየሆነ ስለሄደው የፕረስ ነጻነት ይዞታ» ያካሄደውን ውይይት ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW