በሕወሓት መግለጫ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች
ረቡዕ፣ ጥቅምት 5 2012ማስታወቂያ
ህወሀት ከኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ጋር ካለው የአመላከት እና ተግባር ልዩነት አኳያ የውህደቱ አካል ይሆናል ተብሎ እንደማይጠበቅ አንድ የፖለቲካ ምሁር አመለከቱ።የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ ማእከላይ ኮሚቴ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ካደረገው ስብሰባ በኋላ ባወጣው መግለጫ «ሕጋዊነት የጎደለው» ያለው ውሁድ ፓርቲ የመፍጠሩ ሂደት፣ የሀገሪቱን የፖለቲካ ቀውስ ወደ ባሰ ደረጃ እየገፋ ያለ እና ግንባሩንና ሀገሪቱን ወደ መበተን ሊደርስ የሚችል አደጋ ነውም ብሎታል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስመ ውሁድ ፓርቲ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ውሁድ ፓርቲ የመፍጠር ሳይሆን አዲስ ፓርቲ የማቋቋም ሥራ ነው ሲልም ወቅሷል።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ