1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አስተያየት በኢትዮጵያ የምርጫ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ማሻሻያ ላይ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 27 2016

የሕግ ባለሙያ አቶ ሙስጠፋ ዓብዱ የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት ከፌደራል መንግስቱ ጋር የተፈራረመው ህወሓት፥ ስምምነቱ ከጦርነቱ ጅማሮ በኃላ ፈርሶ የነበረው ሕገመንግስታዊ ስርዓት እንዲመለስ የሚያስገድድ በመሆኑ ያለ የሕግ ማሻሻ ወደ ሕጋዊነት የሚመለስበት ዕድል እንደነበረ ይሞግታሉ።

Äthiopien, Addis Abeba | Äthiopisches Parlament
ምስል Solomon Muchie/DW

አስተያየት በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ማሻሻያ ላይ

This browser does not support the audio element.

ህወሓትን ዳግም ሕጋዊ እውቅና ልያስገኝለት የሚያስችል የተባለ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር ማሻሻያ አዋጅን፥ የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ። የሕግ ባለሙያ የአዋጁ ማሻሻያ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚያበረታታ ብለውታል። 

የትግራዩ ጦርነት ተከትሎ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሕጋዊ የፖለቲካ ፖርቲነት ተዘርዞ፣ በሀገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአሸባሪነት ተፈርጆ የነበረው ህወሓት ከፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት በኃላ ደግሞ የአሸባሪነት ፍረጃው ተነስቶ፣ ወደ ሰላማዊ ፖለቲካ መድረኩ ቢመለስም ሕጋዊነቱ ሳያገኝ ቆይቷል። የተሻሻለው የጸረ ሽብር አዋጅ

የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዛሬ ያፀደቀው እና ህወሓትን ጨምሮ ሌሎች ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የተቀላቀሉ የፖለቲካ ሐይሎችን ሕጋዊነት ያላብሳል ተብሎ የሚጠበቅ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ-ምግባር ማሻሻያ አዋጅ በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበሩ የፖለቲካ ሐይሎች በልዩ ሁኔታ እንዲመዘገቡ የሚያስችል የሕግ ማሻሻያ ተብሎለታል። 

ያነጋገርናቸው የሕግ ባለሙያ አቶ ሙስጠፋ ዓብዱ፥ ዛሬ በፖርላማው የፀደቀው አዋጅ በሰላማዊ ትግል ላልነበሩ ሐይሎች ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ መድረክ የሚመጡበት መልካም ዕድል የሚፈጥር ብለውታል። 

በትግራይ የህወሓት ቢሮምስል Million H. Selassie/DW

የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ከፌደራል መንግስቱ ጋር የተፈራረመው ህወሓት፥ ስምምነቱ ከጦርነቱ ጅማሮ በኃላ ፈርሶ የነበረው ሕገመንግስታዊ ስርዓት እንዲመለስ የሚያስገድድ በመሆኑ ያለ የሕግ ማሻሻ ወደ ሕጋዊነት የሚመለስበት ዕድል እንደነበረ የሕግ ምሁሩ አቶ ሙስጠፋ ዓብዱ ይሞግታሉ። የተሻሻለዉ የኤክሳይዝ ታክስ ግሽበትን ያባብሳል ተባለ

ይህ ማሻሻያ በኢትዮጵያ ሚኒስቴሮች ምክርቤት ባለፈው ዓርብ ይፋ ሲደረግ በኤክስ የማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ሐሳባቸው ያጋሩት የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ሰላምን ለማጠናከር አንድ እርምጃ በትክክለኛ አቅጣጫ ብለውታል። በዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ውሳኔ ዙርያ ከህወሓት ፅሕፈት ቤት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት እስከ ማምሻው ድረስ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።


ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW