1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«አስቸጋሪ ምርጫዎች» ድራማ፥ ክፍል 4

እሑድ፣ መጋቢት 20 2012

ይህ በኮሌራ ወረርሽኝ እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚያተኩረው «አስቸጋሪ ምርጫዎች» በሚል ርዕስ የሚቀርብላችሁ የወንጀል ተፋላሚዎቹ ተከታታይ ድራማ አራተኛ ክፍል ነው።

DW Crime Fighters Serienmotiv „Uneasy choices“

«አስቸጋሪ ምርጫዎች»

This browser does not support the audio element.

ባለፈው ጊዜ የሐይማኖት ወላጆች አቶ ባቢሌ እና ወይዘሮ አበበች ወደቤት ያልተመለሰች ልጃቸውን በሚመለከት አስደንጋጭ ዜና ሰምተው ነበር። ሐይማኖት  በበጎ ፍቃደኝነት ለአካባቢ እና ጤና ጥበቃው ጽሕፈት ቤት  ስትሠራ ነው የከረመችው። ኅብረተሰቡ በሙሉም ለመጪው የዝናብ ወቅት እየተዘጋጀ ነው። የጎርፍ መጥለቅለቅ ወይም ሌላ የኮሌራ ወረርሽኝ እንዳይከሰት ሰግቷል። ታድያ ሃይማኖት በሌለችበት ይህንን እንደምን ይወጡት ይኾን? የአካባቢ እና ጤና ጥበቃው ጽሕፈት ቤት በጉጉት ከመንግሥት ሲጠብቀው የነበረውን የርዳታ ገንዘብ አግኝቶ ይሆን? ሃይማኖት ከመሰወሯ በፊት ከንቲባው እና አለቃዋ አቶ አቡበክር ገንዘብ እንዴት አድርገው እንደሚያጭበረብሩ ሲዶልቱ ሰምታለች። “እውነታውን ፍለጋ” የተሰኘውን የዛሬውን ክፍል የምንጀምረው መርማሪ ፖሊሶቹ ወታደር ፋና እና ወታደር ክፍሌ  የሃይማኖትን ጉዳይ ሲመረምሩ ነው። 

ደራሲ፦ ፒናዶ አዳማ ዋባ
አዘጋጅ፦ ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW