የሶማሊያ መሪዎች ውዝግብ
ሐሙስ፣ መስከረም 6 2014![Somalia Präsident Mohamed Abdullahi Mohamed | Farmajo](https://static.dw.com/image/57632052_800.webp)
ማስታወቂያ
በሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂና በጠቅላይ ሚኒስትር ሞሐመድ ሁሴን ሮብሌ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ በችግር ላይ ያለችው ሀገር ጭርሱን ወደ ባሰ የርስ በርስ ግጭት እንዳትገባ አስግቷል። በተለይ የሶማሊያ መንግሥት የደኅንነት ቢሮ ሰራተኛ ከታገቱ በኋላ ተገድለው መገኘታቸው ያስነሳው ሌላ ውዝግብ ትኩረት ስቧል።የግጭቶችን መንስኤና ሂደት በማጥናት መፍትሄውን የሚጠቁመው ክራይስ ግሩፕ የተባለው ድርጅት እንዳለው የደኅንነት ሠራተኛዋ ግድያ ከሶማሊያ ወታደሮች የውጭ ስልጠና ጋር በተያያዘ የሚያውቁትን መረጃ እንዳያወጡ ለማድረግ የተፈጸመ ሳይሆን እንዳልቀረ አስታውቋል። በግድያው አሸባብ ቢጠረጠርም አሸባብ ግን ውንጀላውን አስተባብሏል። ዛሬ እንደተሰማው ፕሬዝዳንቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሥልጣን በከፊል ገድበዋል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ