1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አሶሳ፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ10 በላይ ተገደሉ

ዓርብ፣ መስከረም 15 2013

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ቤንገዝ ቀበሌ ትናንት ሌሊቱን በደረሰ ጥቃት ቢያንስ 14 ሰዎች መገደላቸው፤ አምስት ደግሞ መታገታቸው ተሰማ። የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት በርካታ ንብረትም በታጣቂዎች በደረሰው ጥቃት ወድሟል።

Karte Äthiopien englisch

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ቤንገዝ ቀበሌ ትናንት ሌሊቱን በደረሰ ጥቃት ቢያንስ 14 ሰዎች መገደላቸው፤ አምስት ደግሞ መታገታቸው ተሰማ። የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት በርካታ ንብረትም በታጣቂዎች በደረሰው ጥቃት ወድሟል። የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን ዛሬ እንደዘገበው ጥቃቱ የተፈጸመበት የቤንጌዝ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ ድርጊቱ መፈጸሙን በማረጋገጥ፤ ጥቃቱ የደረሰው ሌሊት በመሆኑ ለመከላከልም ሆነ አጥፊዎቹን ለመከታተል እንዳልተቻለ ገልጸዋል። የዳንጉር ወረዳ አስተዳዳሪ በበኩላቸው ከጥቃቱ በኋላ ወደስፍራው የፀጥታ አካላት ተንቀሳቅሰው እያጣሩ መሆኑንም ለመገናኛ ብዙሃኑ መግለጻቸው ተጠቅሷል። ዶቼ ቬለም የመተከል ዞን አስተዳደር እንዲሁም የክልሉን የፖሊስ ኮሚሽን፣ የጸጥታና ሰላም ባለሥልጣኖችን ለማግኘት ጥረቱን ቀጥሏል። ትናንት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት በመተከል ዞን በሚገኙ አራት ወረዳዎች የወታደራዊ ዕዝ (ኮማንድ ፖስት) መመሥረቱን የክልሉ አሳውቆ ነበር።

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW