አባ ዉዴ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 12 2000ማስታወቂያ
ሃሚና ፣ አሚና ፣ አባ ዉዴ ፣ አባ ነዝንዝ ወይም ላሊበላ የሚባሉት ሰዎች እነ ማን ናቸዉ፣ ካልለመንን ቁምጥና በሽታ ይይዘናል የሚል እምነት እንዳላቸዉም ይነገራል፣ እርግማናቸዉ ይደርሳል ስለሚባልም በህብረተሰብ ዘንድ ይፈራሉ፣ ይከበራሉ፣ እዉነት ይህ የልመና ስርአት ከባህል ይመደብ ይሆን? አሁን አሁን የኔብጤዉን ከሃሚናዎች መለየት ያስቸግራል፣ በሌላ በኩል የቁምጥና በሽታ መድሃኒት ተገኝቶለታል! በዚህም ምክንያት ይህ አይነቱ የልመና ስርአት የጠፋ ይመስላል የሚሉም አሉ። የእነዚህ ወገኖች ታሪክ ምን ይመስል ይሆን ባለሞያ አነጋግረናል መልካም ቆይታ