1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ፓርላማ የፌደራልና የኦሮምያ ክልል መንግሥታት ለወለጋው ጥቃት ተጠያቂ ተባሉ

ረቡዕ፣ ሰኔ 29 2014

አብን በኦሮሚያ ክልል ለተፈጸሙ የዘር ማጽዳት ሲል የገለፃቸውን ውንጀሎች የሚያጣራ ልዩ ዐቃቤ ሕግ በአዋጅ እንዲቋቋምና የወንጀል ፈፃሚዎች በግልጽ ችሎት እንዲዳኙም ጠይቋል።የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ኢሰመጉ በበኩሉ የወለጋውን ጭፍጨፋ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል መንግሥታት በአስቸኳይ እንዲያስቆሙና አጥፊዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል።

ABIN party statement I   06.07.2022
ምስል Solomon Muchie/DW

አብን፣ ለጭፍጨፋዉ የተወካዮች ምክር ቤት፣ የፌደራልና የኦሮሚያ መንግስትን ወቀሰ

This browser does not support the audio element.

 የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን በተከታታይ የጅምላ ጭፍጨፋ እየተፈፀመበት በሚገኘው በኦሮሚያ ክልል በወለጋ እና አካባቢው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነገግ ጠየቀ። የአካባቢው ነዋሪዎች ታጥቀው ራሳቸውን እንዲከላከሉ እና በፀጥታ ሥራው ላይ በአጋዥነት እንዲሳተፉም የጠየቀው አብን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤትንና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትን ችግሩን ማስቆም ባለመቻል ተጠያቂ መሆናቸውን ገልጿል።ፓርቲው ባለፉት አራት አመታት ተፈጽሟል ላለውና ከሰሞኑም በኦሮሚያ ክልል እየተፈፀመ ለሚገኙ የዘር ማጽዳት ሲል የገለፃቸውን ውንጀሎች የሚያጣራ ልዩ ዐቃቤ ሕግ በአዋጅ እንዲቋቋም እና የወንጀል ፈፃሚዎች በግልጽ ችሎት እንዲዳኙም ጠይቋል።የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ኢሰመጉ በበኩሉ የወለጋውን ጭፍጨፋ የፌዴራል እና የኦሮሚያ ክልል መንግሥታት በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ እና አጥፊዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል።
 ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ተጨማሪ ዘገባ አለው
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW